የተጣራ መረጃ

በአማራ ክልል ሶስት ዞኖች ጦርነት መጀመሩ ተገለጸ

በአማራ ክልል ሶስት ዞኖች ጦርነት መጀመሩ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው “የሕግ ማስከበር ዘመቻ”ን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። ኮሚሽኑ ይህ ድርጊት በሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን አንድምታና ተጽእኖ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑ አስታውቋል። ኮሚሽኑ አደረኩት ባለው ክትትል በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት አለ ብሏል። በተለይም ሸዋ ሮቢት፣ አርማኒያ፣ አንጾኪያ፣ ገምዛ እና ማጀቴ በመከላከያ ሰራዊት እና በአካባቢው ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥና በከባድ መሣሪያ ጭምር የታገዘ ጥቃት መኖሩን ደርሼበታለሁም ብሏል። በዚህ የተኩስ ልውውጥ ምክንያትም በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ከመድረሱ ባለፈ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ በተለያዩ ጊዜያት መዘጋቱን እንዳረጋገጠ ኮሚሽኑ አስታውቋል። በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተወሰኑ…
Read More
አሜሪካ የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞችን ይፋ አደረገች

አሜሪካ የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞችን ይፋ አደረገች

አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ወይም ዲቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ ታስገባለች። ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ድቪ ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ተገልጿል። የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎችም መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ከሚያዚያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ ጽፏል። ኢምባሲው አክሎም በዲቪ ሎተሪ ድረገጽ ላይ በመግባት አመልካቾች ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት ማወቅ ይችላሉም ብሏል። ይህ በዚህ እንዳለም የዲቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁም አሳስቧል። ለዲቪ ሎተሪ ስለማሸነፋቸው እና አለመድረሱን አመልካቾች በራሳቸው…
Read More
አቶ ግርማ የሺጥላ በምስራቅ አማራ ፋኖ መገደላቸውን የአማራ ክልል ገለጸ

አቶ ግርማ የሺጥላ በምስራቅ አማራ ፋኖ መገደላቸውን የአማራ ክልል ገለጸ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ባለፈው ሳምንት ለተገደሉት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ በምሥራቅ አማራ ፋኖ የሚመራው ‹‹ቡድን›› ነው ሲል የገለጸው ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ ነው፡፡  የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ባልታወቁ ግለሰቦች ግድያ እንደተፈጸመባቸው የተገለጸው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሚያዝያ 19፣ 2015 ነበር፡፡ በወቅቱ ግድያውን ይፋ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለግድያው ‹‹ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው›› ያሏቸው ነገር ግን በሥም ያልጠቀሷቸውን አካላት ተጠያቂ አድርገው ነበር፡፡ አክለውም ‹‹ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ…
Read More
ኢትዮጵያ የዩንቨርሲቲ ምሩቃንን ወደ ውጪ ሀገራት ልትልክ መሆኑን ገለጸች

ኢትዮጵያ የዩንቨርሲቲ ምሩቃንን ወደ ውጪ ሀገራት ልትልክ መሆኑን ገለጸች

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 85 ሺህ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለመላክ አቅዶ 56 ሺህ ዜጎችን ወደ ውጪ ሀገራል ልኬያለሁ ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ስድስት ሚሊዮን ዜጎች በስራ ፈላጊነት መመዘገባቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል። የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፤ በስራ እድል ፈጠራ፣ በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና እንዲሁም በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ላይ መስሪያ ቤታቸው ያከናወናቸውን ስራዎች ለፓርላማው አብራርተዋል። የሚኒስትሯን…
Read More
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደለ

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደለ

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ መገደላቸው ተገለጸ። የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል ተብሏል። የአቶ ግርማን ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባወጡት የሀዘን መግለጫ አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በሀዘን መግለጫቸው " ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም " ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው " ሲሉም ገልጸዋል። "ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው።…
Read More
የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በሱዳን ካርቱም ተገደለ

የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በሱዳን ካርቱም ተገደለ

በሱዳን ለ11ኛ ቀን በዘለቀው ጦርነት የሟቾች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ ይገኛል። ጦርነቱ በሱዳን ብሔራዊ ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ሀይል መካከል ሲሆን አንዱ ባንዱ ላይ ድል መቀዳጀቱ እየተገለጸ ይገኛል። ጦርነቱ እንዲቆም በርካቶች እያሳሰቡ ቢሆንም ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ ማቆማቸውን ቢናገሩም ጦርነቱ ግን ቆሞ አያውቅም ተብሏል። የግብጽ መንግሥት እንዳለው በሱዳን ካርቱም የነበራት ወታደራዊ አታቼ መገደሉን አስታውቃለች። ይሁንና ይህ የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በማን እንደተገደለ እስካሁን አልተገለጸም። አሜሪካ፣ የአውሮፓ ሀገራት፣ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎችም ሀገራት ዲፕሎማቶቻቸውን ከሱዳን ያስወጡ ሲሆን ቀሪ ዜጎቻቸውን ግን እስካሁን አላስወጡም። በርካታ ዜጎች በካርቱም ጦርነቱ መቀጠሉን ተከትሎ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በኩል አድርገው በመውጣት ላይ እንደሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያም በመተማ በኩል ከሱዳን የሚመጡ…
Read More
በሚዛን አማን ሁለት ህጻናት በመብረቅ አደጋ ህይወታቸው አለፈ

በሚዛን አማን ሁለት ህጻናት በመብረቅ አደጋ ህይወታቸው አለፈ

በኢትዮጵያ ሁለት ህጻናት በመብረቅ አደጋ ህይወታቸው አለፈበመብረቅ አደጋ የአምስት እና የሰባት አመት እድሜ ያላቸዉ የሁለት ታዳጊ ህፃናት ህይወት ማለፉ ተገልጿል። በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በመብረቅ አደጋ የሁለት ታዳጊ ህፃናት ህይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በከተማው አዲስ ከተማ ቀበሌ ልዩ ስሙ ብርሃን አዲስ ከተማ ሠፈር ከቀኑ 8፡30 የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው መብረቅ የሁለት ህፃናት ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል። አደጋው የደረሰው ሶስት ህጻናት ውሃ ለመቅዳት ወንዝ በሄዱበት ወቅት ዝናብ በመዝነቡ ለመጠለል ዛፍ ስር በሚገኝ ድንጋይ ላይ በተቀመጡበት ወቅት ነው። በዚህ የመብረቅ አደጋ ምክንያትም የሁለቱ ህፃናት ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በመብረቅ አደጋ ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጎች…
Read More
የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አሳየ

የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አሳየ

የኢትዮጵያ የዘጠኝ ወራት የወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አሳየ። የንግድ እና ቀጠናዊ ውህደት ሚንስቴር እንደገለጸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር። ይሁንና የተገኘው ገቢ ግን በአንድ ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል ተብሏል። ለገቢው መቀነስ የጸጥታ ችግሮች፣ ህገወጥ ንግድ፣ የዓለም ንግድ መቀዛቀዝ እና የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል። ከተገኘው ገቢ ውስጥም ግብርና የ77 በመቶ ድርሻ ሲያዝ ቀሪው ማዕድን፣ ኢንዱስትሪ እና ኤሌክትሪክ ሽያጭ እንደሆኑ ሚንስቴሩ ገልጿል ባለፉት ሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ የቆየችው ኢትዮጵያ የወጪ ንግዷ ተዳክሞ የቆየ ሲሆን በአሜሪካ የተጣለባት ማዕቀብ፣ ህገወጥ የማዕድን ገበያ መስፋፋት ለወጪ ንግዱ ዋነኛ ችግሮች…
Read More
በሱዳን ያሉ የውጭ ዜጎችን በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ተጀመረ

በሱዳን ያሉ የውጭ ዜጎችን በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ተጀመረ

ኢትዮ ነጋሪ፣ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም:- ሀገራት ዜጎቻቸውን እያስወጡ ያሉት በጋላባት-መተማ በኩል ነው ተብሏል ዜጎችን የማስወጣት ስራው በካርቱም ካለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጋር በመነጋገር ነው በሱዳ. ያሉ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ተጀመረ የተለያዩ ሀገራት በሱዳን ያሉ ዜጎቻቸውን በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ማስወጣት ጀምረዋል። በሱዳን ብሔራዊ ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ መካከል የተጀመረው ጦርነት ስምንተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። ለኢድ በዓል ተብሎ የሶስት ቀን ተኩስ አቁም ቢደረግም ጦርነቱ ዛሬም እንደቀጠለ ነው ተብሏል። ይህ በዚህ እንዳለ የተለያዩ ሀገራት በሱዳን የሚገኙ ዜጎቻቸውን ለማስወጣት ትረቶች ላይ ይገኛሉ። ከካርቱም ዜጎቻቸውን በአየር ትራንስፖርት ለማውጣት ያልተሳካላቸው ሀገራት በየብስ ትራንስፖርት በኢትዮጵያ ድንበር በኩል እያስወጡ መሆኑን ሰምተናል። ሀገራቱ…
Read More
ኢትዮጵያ ጦሯን ወደ ሱዳን አስገብታለች መባሉን አስተባበለች

ኢትዮጵያ ጦሯን ወደ ሱዳን አስገብታለች መባሉን አስተባበለች

በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችው ሱዳን እስካሁን የተገደሉ ዜጎች ቁጥር ከ350 በላይ አሻቅቧል። ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሱዳን ግዛት ገብቶ ወረራ ፈጽሟል የሚሉ ዜናዎች በበርካታ የሱዳን ሚዲያዎች ተዘህበዋል። ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ምንም አይነት ወታደር ወደ ሱዳን ግዛት አለማስገባቷን አስታውቃለች። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ "በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ግጭት መቀስቀስ የሚፈልጉ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመግለጫቸው አንዳንድ አካላት የኢትዮጵያ እና ሱዳን ግንኙነትን ለማበላሸት በማሰብ፣ "ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ሱዳን ውስጥ አስገብታለች በማለት ሐሰተኛ መረጃ እያሠራጩ ነው" ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግብ ቢኖራቸውም ልዩነታቸው በንግግር ይፈታል ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል። "ኢትዮጵያ አሁን ሱዳን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ለድንበር…
Read More