02
May
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ባለፈው ሳምንት ለተገደሉት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ በምሥራቅ አማራ ፋኖ የሚመራው ‹‹ቡድን›› ነው ሲል የገለጸው ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ ነው፡፡ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ባልታወቁ ግለሰቦች ግድያ እንደተፈጸመባቸው የተገለጸው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሚያዝያ 19፣ 2015 ነበር፡፡ በወቅቱ ግድያውን ይፋ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለግድያው ‹‹ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው›› ያሏቸው ነገር ግን በሥም ያልጠቀሷቸውን አካላት ተጠያቂ አድርገው ነበር፡፡ አክለውም ‹‹ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ…