የተጣራ መረጃ

ተመድ በቶርች ጉዳይ ኢትዮጵያን ሊገመግም መሆኑን አስታወቀ

ተመድ በቶርች ጉዳይ ኢትዮጵያን ሊገመግም መሆኑን አስታወቀ

የተባበሩት መንግታት ድርጅት በፈረንጆቹ 1984 ላይ በእስረኞች የሚፈጸሙ ስቃዮችን ወይም ቶርቸርን ለመከላከል በማሰብ ስምምነት አዘጋጅቶ ነበር። ይህን ስምምነት ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ሀገራት የተቀበሉት ሲሆን ትግበራው ግን ከቦታ ቦታ ይለያያል። የዚህ ስምምነት አዘጋጅ የሆነው ተመድ ስምምነቱን የተቀበሉ ሀገራት ህጉን እንዴት እየተገበሩት እንደሆነ ሊገመግም መሆኑን ለዓልዐይን በላከው መግለጫ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ፣ ኮሎምቢያ፣ ብራዚል፣ ካዛኪስታን፣ ስሎቫኪያ እና ሉግዘምበርግ ደግሞ የሚገመገሙ ሀገራት ናቸው ተብሏል። 10 አባላት ያሉት የተመድ ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ሀገራቱን በጀኔቫ እንደሚገመግሙም ተገልጿል። ይህ የባለሙያዎች ቡድንም የጸረ ቶርቸር ህግ ትግበራው ግምገማው የተገምጋሚ ሀገራት ተወካዮች፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት ይገኛሉ ተብሏል። ግምገማውም ከሚያዚያ 9 ቀን እስከ…
Read More
በደብረ ብርሃን ውሃ ተበክሏል እየተባለ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑ ተገለጸ

በደብረ ብርሃን ውሃ ተበክሏል እየተባለ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑ ተገለጸ

የደብረብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት መሰረት መንገሻ እንደገለጹት ከትላንት ጀምሮ መርዝ ተጨምሮበት ውሃ ተበክሏል እየተባለ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ተቋማቸው አንዱ ተግባሩ የሚያመርተውን ውሃ ጥራት አረጋግጦ ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት ሃላፊነታቸው በመሆኑን ባለሙያዎች እሁድ ቅዳሜን እና የበዓላትን ቀናት ጭምር አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖች ታጥረው የሚጠበቁ ከመሆኑም በላይ ሁል ጊዜ በባለሙያ ክትትል እየተደረገላቸው ውሃው በባለሙያ ጥራቱ ተረጋግጦ ለደንበኞች እንደሚሰራጭ አረጋግጠዋል፡፡ የፀጥታ ችግር ሲከሰት ደግሞ በልዩ ሁኔታ ጥበቃና ክትትል እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል፡፡ ችግር ካጋጠመም ውሃው እንደማይለቀቅ ጠቅሰው ህብረተሰቡ የውሃ ተቋሙ የሚያደርገውን ጥንቃቄ በአግባቡ ተረድቶ በአሉባልታ ወሬ እንዳይረበሽ መክረዋል፡ ውሃው 100 ፐርሰንት ንጹህ መሆኑን ስራ አስኪያጇ መልዕክታቸውን…
Read More
እነ ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በነጻ ተሰናበቱ

እነ ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በነጻ ተሰናበቱ

ዶ/ር ሙሉቀን ሐብቱን ጨምሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው አምስት ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሐብቱን ጨምሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው አምስት ግለሰቦች በነጻ አሰናብቷቸዋል፡፡  ፍርድ ቤቱ ብይኑን የሰጠው ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 4፤ 2015 በዋለው ችሎት ነው፡፡  በዚሁ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ ተከሳሽ በሌሉበት ጥፋተኛ ሲባሉ፤ ቀሪ አምስት ተከሳሾች ደግሞ የተከሰሱበት ድንጋጌ ተቀይሮ እንዲከላከሉ በፍርድ ቤቱ በይኗል። ችሎቱ አምስት ተከሳሾችን በነጻ ያሰናበተው፤ “ዐቃቤ ህግ ባቀረበው የሰው…
Read More
ኢትዮጵያ በህገ ወጥ ማዕድን ማውጣት ስራ ተሰማርተው የተገኙ 90 የውጭ ዜጎችን አሰረች

ኢትዮጵያ በህገ ወጥ ማዕድን ማውጣት ስራ ተሰማርተው የተገኙ 90 የውጭ ዜጎችን አሰረች

የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ዜጎች በኢትዮጵያ በማእድን ማውጣት ስራ ተሰማርተው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡ በጋምቤላ ክልል በህገ ወጥ መንገድ ወርቅን ጨምሮ ማእድን ማውጣት ሰራ ላይ የተሰማሩ 45 የውጭ ሀገራት ዜጎች መያዛቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል። የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ በክልሉ 3 ኢትዮጵያውያንም ተይዘዋል ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 47 የውጭ ዜጎች ወርቅን ጨምሮ በማእድን ማውጣት ስራ ላይ ተሰማርተው ሲያዙ 9 የግል ማህበራትና 7 ኢትዮጵያውያንም በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብላል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከሰሞኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳሉት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በህገ ወጥ ማእድን ንግድ መታወኩን ተናግረው ነበር። እነዚህን ህገወጥ የማእድን አዘዋዋሪዎች ለመቆጣጠር የጸጥታ ሀይል እናሰማራለን ሲሉ ለምክር ቤቱ…
Read More
መንግሥት የአማራ ልዩ ሀይልን ጨምሮ የሁሉንም ክልል ልዩ ሀይሎች ትጥቅ እያስፈታ መሆኑን ገለጸ

መንግሥት የአማራ ልዩ ሀይልን ጨምሮ የሁሉንም ክልል ልዩ ሀይሎች ትጥቅ እያስፈታ መሆኑን ገለጸ

መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅ የሚያስችል አንድ ጠንካራ የተማከለ ሠራዊት ለመገንባት አቅጣጫ ማስቀመጡን ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። በዚህ መሠረት የየክልሉን ልዩ ኃይሎች ወደ ተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ መጀመሩን አሳውቋል። በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የልዩ ኃይል አባላት እንደ ምርጫቸውና እንደ ፍላጎታቸው ፣በመከላከያ፣ በፌደራል ፖሊስ፣በክልል ፖሊስ አባልነት መካተት ይችላሉ ብሏል። በዚህ ሐሳብ ላይም ከልዩ ኃይል አመራሮችና አባላት ጋር ከመግባባት ላይ መደረሱን ገልጿል። ቀደም ብሎም በሁሉም ክልል አመራሮች ጥናት ተደርጎበት፣ በተገኘው ውጤት ያለምንም ልዩነት ውሳኔው ስምምነት ተደርሶበታል ሲል አስታውሷል። የክልል ልዩ ኃይልን በተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች የማካተት ውሳኔና የተግባር እንቅስቃሴ በጥናት ላይ ተመሥርቶ የሚከናወን ነው ያለው መንግስት " ይህ…
Read More
ኢትዮጵያዊው ወጣት በሚያምነው ፈረሱ ተገደለ

ኢትዮጵያዊው ወጣት በሚያምነው ፈረሱ ተገደለ

በደቡብ ኢትዮጵያ አንድ ወጣት ለጭነትና ለመጓጓዣ በሚጠቀምበት ፈረስ ህይወቱ አልፏል። በደቡብ ክልል ጌድኦ ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ ለጭነትና ለመጓጓዣ በሚጠቀምበት የገዛ ፈረሱ የአንድ ወጣት ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። ወጣት ቅጤሳ አለሙ በጌድኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ ከሚኖርበት የገጠር ቀበሌ እንጨት ጭኖ ወደ ከተማ በማምጣት እንጨቱን ሸጦ ወደ ቤቱ በመመለስ ላይ ነበር። ይህ የ26 ዓመት ወጣት ፈረሱ ላይ ተቀምጦ ወደ ቤቱ በመመለስ ላይ እያለ ፈረሱ በሞተር ብስክሌት ድምፅ ደንብሮ ወጣቱን መሬት ላይ ጥሎታል ተብሏል። ወጣቱ ከፈረሱ አንገት ላይ የነበረ ረዥም ገመድ በወገቡ እንደመቀነት ታጥቆት ኖሮ  በርግጎ በሚሮጠዉ ፈረስ መሬት ለመሬት እየተጎተተ ከድንጋይና ከግንድ ጋር ይላተማል። በአካባቢዉ ህብረተሰብ ትጋትና ርብርብ እንደምንም ፈረሱን ማስቆም…
Read More
አቶ ሮባ መገርሳ ከሀላፊነት ተነሱ

አቶ ሮባ መገርሳ ከሀላፊነት ተነሱ

የኢትዮጵያ ባህር ሎጅስቲክስ አገልግሎትን ላለፉት አምስት ዓመታት በሀላፊነት የመሩት አቶ ሮባ መገርሳ ከሀላፊነት ተነስተዋል። በዚህ ተቋም ከባለሙያነት ጀምሮ ያገለገሉት አቶ ሮባ ለምን ከሀላፊነት እንደተነሱ ይፋ አልተደረገም። በአቶ ሮባ ቦታም በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) ከትናንት መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ መሾማቸውን ኢትዮ ነጋሪ ከተቋሙ የኮሙንኬሽን ሀላፊ አቶ ደምሰው በንቲ አረጋግጣለች። አዲሱ ሀላፊ ከዚህ በፊት በኦሮሚያ ክልል ከወረዳ እስከ ፌደራል ተቋማት በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ መስራታቸው ተገልጿል።
Read More
የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች ተገደሉ

የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ። የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ ዛሬ ጠዋት በመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች መገደላቸውን የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል። ኃላፊው ወደ ስራ ለመሄድ ከቤታቸው በወጡበት ጊዜ በተተኮሰባቸው ጥይት እንደተገደሉም ነው የከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት በማህበራዊ ገጽ ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው። አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ከመሾማቸው አስቀድሞ የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊነትን ጨም በተለያዩ ስፍራዎች ላይ ሲያገለግሉ መቆየታቸውም ተገልጿል። የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ…
Read More
መንግሥት በህወሀት አመራሮች ላይ የመሰረተውን ክስ አቋረጠ።

መንግሥት በህወሀት አመራሮች ላይ የመሰረተውን ክስ አቋረጠ።

መንግሥት በህወሀት አመራሮች ላይ የመሰረተውን ክስ አቋረጠ። የፍትህ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ በፌዴራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) መሃከል በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት ከግጭቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወንጀሎች ተጠያቂነት በተመለከተ ያለውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ሊታዩ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብላል። በመሆኑም በወንጀል ተጠርጥረዉ ክስ ቀርቦባቸዉ የነበሩ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮችን ክስ ማቋረጡን ሚንስቴሩ አስታውቃል። ክሱ የተቋረጠላቸው ተከሳሾች ጉዳያቸዉ በቀጣይ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ እንደሚታይም ተገልጿል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀርቦ በክርክር ሂደት ላይ ይገኙ የነበሩ የወንጀል ክሶች በአዋጅ 943/2008 አንቀጽ 6 (3) (ሠ) መሰረት መነሳታቸውን ሚንስቴሩ ገልጻል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት…
Read More
የአማራ ክልል ከአገው ሸንጎ ጋር ሲያደርገው የነበረው ውይይት አለመሳካቱ ተገለጸ

የአማራ ክልል ከአገው ሸንጎ ጋር ሲያደርገው የነበረው ውይይት አለመሳካቱ ተገለጸ

የአገው ሸንጎ በህወሃት ድጋፍ የአገው ክልልን ለመመስረት የትጥቅ ትግል እያደረገ ያለ ፓርቲ መሆኑ ይታወሳል፡፡ የአማራ ክልል መንግስትም ከአገው ሸንጎ ታጣቂዎች ጋር የሰላም ውይይት በማድረግ ላይ መሆኑን የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ይልቃል ከፋለ ከሁለት ሳምንት በፊት ምክር ቤት ላይ መናገራቸው አይነጋም፡፡ ይሁንና ይህ የሰላም ውይይት አለመሳካቱን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ስቡህ ገበያው ተናግረዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ላለፉት 21 ወራት በህወሓት እና በአገው ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች ይዞታ ስር የቆየችውን የአበርገሌ ወረዳ ዋና ከተማን፤ የመከላከያ ሰራዊት መልሶ ተቆጣጥሯል። የመከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስር ወደምትገኘው “ንየር አቑ” ከተማ የገባው፤ ታጣቂዎቹ አካባቢውን በትላንትናው ዕለት ለቅቀው ከወጡ በኋላ እንደሆነ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ…
Read More