disinformation

በደብረ ብርሃን ውሃ ተበክሏል እየተባለ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑ ተገለጸ

በደብረ ብርሃን ውሃ ተበክሏል እየተባለ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑ ተገለጸ

የደብረብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት መሰረት መንገሻ እንደገለጹት ከትላንት ጀምሮ መርዝ ተጨምሮበት ውሃ ተበክሏል እየተባለ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ተቋማቸው አንዱ ተግባሩ የሚያመርተውን ውሃ ጥራት አረጋግጦ ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት ሃላፊነታቸው በመሆኑን ባለሙያዎች እሁድ ቅዳሜን እና የበዓላትን ቀናት ጭምር አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖች ታጥረው የሚጠበቁ ከመሆኑም በላይ ሁል ጊዜ በባለሙያ ክትትል እየተደረገላቸው ውሃው በባለሙያ ጥራቱ ተረጋግጦ ለደንበኞች እንደሚሰራጭ አረጋግጠዋል፡፡ የፀጥታ ችግር ሲከሰት ደግሞ በልዩ ሁኔታ ጥበቃና ክትትል እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል፡፡ ችግር ካጋጠመም ውሃው እንደማይለቀቅ ጠቅሰው ህብረተሰቡ የውሃ ተቋሙ የሚያደርገውን ጥንቃቄ በአግባቡ ተረድቶ በአሉባልታ ወሬ እንዳይረበሽ መክረዋል፡ ውሃው 100 ፐርሰንት ንጹህ መሆኑን ስራ አስኪያጇ መልዕክታቸውን…
Read More