Shipment

አቶ ሮባ መገርሳ ከሀላፊነት ተነሱ

አቶ ሮባ መገርሳ ከሀላፊነት ተነሱ

የኢትዮጵያ ባህር ሎጅስቲክስ አገልግሎትን ላለፉት አምስት ዓመታት በሀላፊነት የመሩት አቶ ሮባ መገርሳ ከሀላፊነት ተነስተዋል። በዚህ ተቋም ከባለሙያነት ጀምሮ ያገለገሉት አቶ ሮባ ለምን ከሀላፊነት እንደተነሱ ይፋ አልተደረገም። በአቶ ሮባ ቦታም በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) ከትናንት መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ መሾማቸውን ኢትዮ ነጋሪ ከተቋሙ የኮሙንኬሽን ሀላፊ አቶ ደምሰው በንቲ አረጋግጣለች። አዲሱ ሀላፊ ከዚህ በፊት በኦሮሚያ ክልል ከወረዳ እስከ ፌደራል ተቋማት በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ መስራታቸው ተገልጿል።
Read More