14
Apr
የተባበሩት መንግታት ድርጅት በፈረንጆቹ 1984 ላይ በእስረኞች የሚፈጸሙ ስቃዮችን ወይም ቶርቸርን ለመከላከል በማሰብ ስምምነት አዘጋጅቶ ነበር። ይህን ስምምነት ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ሀገራት የተቀበሉት ሲሆን ትግበራው ግን ከቦታ ቦታ ይለያያል። የዚህ ስምምነት አዘጋጅ የሆነው ተመድ ስምምነቱን የተቀበሉ ሀገራት ህጉን እንዴት እየተገበሩት እንደሆነ ሊገመግም መሆኑን ለዓልዐይን በላከው መግለጫ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ፣ ኮሎምቢያ፣ ብራዚል፣ ካዛኪስታን፣ ስሎቫኪያ እና ሉግዘምበርግ ደግሞ የሚገመገሙ ሀገራት ናቸው ተብሏል። 10 አባላት ያሉት የተመድ ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ሀገራቱን በጀኔቫ እንደሚገመግሙም ተገልጿል። ይህ የባለሙያዎች ቡድንም የጸረ ቶርቸር ህግ ትግበራው ግምገማው የተገምጋሚ ሀገራት ተወካዮች፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት ይገኛሉ ተብሏል። ግምገማውም ከሚያዚያ 9 ቀን እስከ…