Specialforces

ኢትዮጵያ ብሔራዊ የውትድርና ፖሊሲ አጸደቀች

ኢትዮጵያ ብሔራዊ የውትድርና ፖሊሲ አጸደቀች

ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸውና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል አዲስ አዋጅ ፀድቋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት አዋጅን አጽድቋል። ምክር ቤቱ ከትናንት በስቲያ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ መንግስት አዘጋጅቶ ያቀረበውን የተሻሻለ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ዲማ ነገዎ እንደተናገሩት፤ ተማሪዎች በፈቃዳቸው በመደበኛ መከላከያ ሰራዊት ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ሃይል አባል የሚሆኑ ከሆነ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ተያያዥ መብቶችንና ጥቅሞች እንዲጠብቁላቸው ያደርጋል ብለዋል፡፡ በመንግስት ተዘጋጅቶ የቀረበው የተሻሻለ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ የተጣለበትን ሀገርን…
Read More
መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ ኢሰመኮ አሳሰበ

መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ ኢሰመኮ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰሞኑ የክልል ልዩ ሀይሎችን በሚመለከት በተፈጠሩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። ተቋሙ እንዳለው የልዩ ሀይሎችን መልሶ የማደራጀትን ውሳኔ ትግበራ በውይይትና የሰዎችን ሰብአዊ መብቶች አደጋ ላይ በማይጥል ሁኔታ ሊከውን ይገባል ሲል አሳስቧል ኢሰመኮ መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን በፌዴራልና በክልል መደበኛ የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ መልሶ ለማደራጀት ያሳለፈውን ውሳኔና ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ተቃውሞዎች፣ የጸጥታ መደፍረስ እና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሱ ግጭቶችንና ጉዳቶችን በተመለከተ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ኮሚሽኑ በተለይም በቆቦ፣ በባሕር ዳር፣ በወረታ፣ በኮምቦልቻ፣ በደብረ ብርሃን እና በመራዊ የተቃውሞ ሰልፎች፣ መንገድ መዘጋት፣ የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በጸጥታ ኃይሎች መካከል ፍጥጫዎች የተከሰቱ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች…
Read More
መንግሥት የአማራ ልዩ ሀይልን ጨምሮ የሁሉንም ክልል ልዩ ሀይሎች ትጥቅ እያስፈታ መሆኑን ገለጸ

መንግሥት የአማራ ልዩ ሀይልን ጨምሮ የሁሉንም ክልል ልዩ ሀይሎች ትጥቅ እያስፈታ መሆኑን ገለጸ

መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅ የሚያስችል አንድ ጠንካራ የተማከለ ሠራዊት ለመገንባት አቅጣጫ ማስቀመጡን ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። በዚህ መሠረት የየክልሉን ልዩ ኃይሎች ወደ ተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ መጀመሩን አሳውቋል። በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የልዩ ኃይል አባላት እንደ ምርጫቸውና እንደ ፍላጎታቸው ፣በመከላከያ፣ በፌደራል ፖሊስ፣በክልል ፖሊስ አባልነት መካተት ይችላሉ ብሏል። በዚህ ሐሳብ ላይም ከልዩ ኃይል አመራሮችና አባላት ጋር ከመግባባት ላይ መደረሱን ገልጿል። ቀደም ብሎም በሁሉም ክልል አመራሮች ጥናት ተደርጎበት፣ በተገኘው ውጤት ያለምንም ልዩነት ውሳኔው ስምምነት ተደርሶበታል ሲል አስታውሷል። የክልል ልዩ ኃይልን በተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች የማካተት ውሳኔና የተግባር እንቅስቃሴ በጥናት ላይ ተመሥርቶ የሚከናወን ነው ያለው መንግስት " ይህ…
Read More
በአማራ ክልል ልዩ ኃይልን እና በፌደራል የጸጥታ ኃይሎች መካከል ውጥረት መፈጠሩ ተገለጸ

በአማራ ክልል ልዩ ኃይልን እና በፌደራል የጸጥታ ኃይሎች መካከል ውጥረት መፈጠሩ ተገለጸ

የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በግዴታ ትጥቅ ለማስፈታት እንቅስቃሴ በመጀመሩ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች፤ በክልሉ ልዩ ኃይል እና በፌዴራል የጸጥታ ተቋማት መካከል ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አስታወቀ፡፡ የክልሉን ልዩ ኃይል ያለ በቂ ዝግጅት፣ ውይይት፣ የጋራ መግባባትና መተማመን ሳይደረስ በድንገት እና ያለበቂ የጸጥታ ዋስትና ለማፍረስ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ እና ውሳኔውን ለማስፈጸም እየሄደበት ያለው መንገድ ኃላፊነት የጎደለው መሆኑን አብን አስታውቋል፡፡ ጉዳዩ በአማራ ክልል ብቻ ሳይወሰን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አለመረጋጋት የሚፈጥር፣ ክልሉን እና  ኢትዮጵያን ወደ ሌላ የቀውስ አዙሪት የሚከት አደገኛ አካሄድ መሆኑን አብን ለፌዴራሉ መንግሥትና ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አሳስቧል፡፡ በመሆኑም፣ የገዥው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ውሳኔውን በአፋጣኝ እንዲቀለብስ እና ከአማራ…
Read More