03
Aug
በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በሁለቱ አካላት መካከል ውጊያ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ከነዋሪዎች አረጋግጠናል፡፡ በክልሉ ኢንተርኔት ለምን እንደተቋረጠ ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት እስካሁን ያሉት ነገር የለም፡፡ ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በቴሌግራም ላይ እገዳ የጣለች ሲሆን መተግበሪያው በቪፒኤን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት መባባሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ እና ጎንደር የሚያደርጋቸውን በረራዎች መሰረዙ ይታወሳል፡፡ የስፔን፣ ፖላንድ እና በርካታ ሀገራት ኢምባሲዎች ዜጎቻቸው ወደ አማራ ክልል እንዳይጓዙ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡ ከወራት በፊት በኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አጋጥሟት የነበረዉን የመከፋፈል ድርጊትና የጳጳሳት ሹመነትን…