28
Mar
ጠቅላይ ሚኒስትር የመንግስታቸውን የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡ ከአንድ የምክር ቤት አባልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዜጎችን ደህንነት እና የሀገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ ዝቅተኛው የመንግስት ኃላፊነት ቢሆንም ይህንን እያደረጉ እንዳልሆነ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ፣ ቤታቸው ይፈርሳል፣ ንብረታቸው ይወድማል የሀገር ሉዓላዊነትን በሚዳፈር መልኩ የጎረቤት ሀገራት ሰራዊቶች በኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ፣ እና ደቡብ ምዕራብ ወሰኖች በርከታ ኪሎ ሜትሮችን ዘልቀው በመግባት ወረራ ፈፅመዋል ሲሉም ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ ቀርቦባቸዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ ደጋግሞ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ስለሚገደሉ ዜጎች፣ ስለሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ወንጀሎች ፣ መፈናቀሎች፣ ግድያዎች ፣ ቤት መፍረሶች…