ጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አህመድ ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር የመንግስታቸውን የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡

ከአንድ የምክር ቤት አባልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዜጎችን ደህንነት እና የሀገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ ዝቅተኛው የመንግስት ኃላፊነት ቢሆንም ይህንን እያደረጉ እንዳልሆነ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡

ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ፣ ቤታቸው ይፈርሳል፣ ንብረታቸው ይወድማል የሀገር ሉዓላዊነትን በሚዳፈር መልኩ የጎረቤት ሀገራት ሰራዊቶች በኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ፣ እና ደቡብ ምዕራብ ወሰኖች በርከታ ኪሎ ሜትሮችን ዘልቀው በመግባት ወረራ ፈፅመዋል ሲሉም ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ ቀርቦባቸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ ደጋግሞ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ስለሚገደሉ ዜጎች፣ ስለሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ወንጀሎች ፣ መፈናቀሎች፣ ግድያዎች ፣ ቤት መፍረሶች በሪፖርቱ በተደጋጋሚ ቢያቀርብም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ግን ችግሮችን አልፈታም።

በኢትዮጵያ አሁን ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የዜጎች ደህንነት እና የሀገር ልዑላዊነት ዋና ስጋት ምንጭ የሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት እንደሆነም ተገልጿል።

በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስታቸው የዜጎችን ችግሮች እየፈቱ እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን እየሰጠ ባለመሆኑ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ተጠይቀዋል፡፡

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከህዝብ በተነሳ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ምክንያት ስልጣናቸውን በራሳቸው ፈቃድ መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም ከአምስት ዓመት በፊት አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው የተሸሙ ቢሆንም ከፍተኛ የህዝብ ትችቶችን እየተነሳባቸው ይገኛል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *