resignation

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳይሬክተር ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳይሬክተር ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጂማ ዲልቦ በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። ዳይሬክተሩ ከአራት ዓመታ በላይ ከመሩት ተቋም ስራቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ በመንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ኃላፊ ስራቸውን ለምን እንደለቀቁ ያሉት ነገር የለም። ጂማ ዲልቦ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ዘርፉ ከነበረበት ድባቴ ወጥቶ ለሀገር ልማትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አስተዋጽኦ ማበርከት መጀመሩ በቀጣይ ዓመታት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በጦርነት ምክንያት የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ቁጥር እያደገ የመጣ ቢሆንም በዛው ልክ ግን ሰራተኞቻቸው እየተገደሉባቸው መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ36 በላይ ለተቸገሩ ዜጎች ድጋፍ ለማድረስ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ እንደተገደሉ ተገልጿል።…
Read More
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ካቢኔያቸውን በትነው ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ካቢኔያቸውን በትነው ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄዎች በመቀበል ላይ ናቸው። የባህርዳር ህዝብን ወክለው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያሉት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጥያቄ አቅርበዋል።የአብን ተወካዩ እንዳሉት "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢኮኖሚዉ ታሟል፣ ወጣቶች ሀገራቸዉ ዉስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ምርጫቸዉ አድርገዋል" ብለዋል። "ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ ፣ ብልጽግና መራሹ ፓርቲ ሀገሪቱ ከገባችበት ቅርቃር ማዉጣት አልቻለም" ያሉት የምክር ቤቱ አባሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ አስተዳደር እንዲያስረክቡ ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጠይቀዋል። ሌላኛው የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አዳነ ተሾመ በበኩላቸው " ዜጎችን በማገት በሚሊዮን ገንዘብ መጠየቅ የዜጎችን ሰላም ወጥቶ መግባት ጥያቄ ዉስጥ ከትቶታል። በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ…
Read More
ጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አህመድ ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ

ጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አህመድ ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር የመንግስታቸውን የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡ ከአንድ የምክር ቤት አባልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዜጎችን ደህንነት እና የሀገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ ዝቅተኛው የመንግስት ኃላፊነት ቢሆንም ይህንን እያደረጉ እንዳልሆነ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ፣ ቤታቸው ይፈርሳል፣ ንብረታቸው ይወድማል የሀገር ሉዓላዊነትን በሚዳፈር መልኩ የጎረቤት ሀገራት ሰራዊቶች በኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ፣ እና ደቡብ ምዕራብ ወሰኖች በርከታ ኪሎ ሜትሮችን ዘልቀው በመግባት ወረራ ፈፅመዋል ሲሉም ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ ቀርቦባቸዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ ደጋግሞ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ስለሚገደሉ ዜጎች፣ ስለሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ወንጀሎች ፣ መፈናቀሎች፣ ግድያዎች ፣ ቤት መፍረሶች…
Read More