06
Jul
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄዎች በመቀበል ላይ ናቸው። የባህርዳር ህዝብን ወክለው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያሉት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጥያቄ አቅርበዋል።የአብን ተወካዩ እንዳሉት "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢኮኖሚዉ ታሟል፣ ወጣቶች ሀገራቸዉ ዉስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ምርጫቸዉ አድርገዋል" ብለዋል። "ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ ፣ ብልጽግና መራሹ ፓርቲ ሀገሪቱ ከገባችበት ቅርቃር ማዉጣት አልቻለም" ያሉት የምክር ቤቱ አባሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ አስተዳደር እንዲያስረክቡ ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጠይቀዋል። ሌላኛው የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አዳነ ተሾመ በበኩላቸው " ዜጎችን በማገት በሚሊዮን ገንዘብ መጠየቅ የዜጎችን ሰላም ወጥቶ መግባት ጥያቄ ዉስጥ ከትቶታል። በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ…