14
Jun
ኬንያ የአፍሪካ ሀገራት የእርስ በርስ ግብይት ሲፈጽሙ እና አገልግሎት ሲለዋወጡ በራሳቸው ገንዘብ ክፍያ መፈጸም እንዲጀምሩ ጠይቃለች። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ ጅቡቲ ያመሩት የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አፍሪካ በዶላር ላይ ያላት ጥገኝነት ይብቃ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። “ከጂቡቲ እቃ ገዝተን በዶላር የምንከፍለው ለምንድን ነው? ለምን? ምንም ምክንያት የለም” ያሉት ፕሬዝዳንት ሩቶ ጂቡቲም ሆነች ኬንያ የእርስ በርስ ግብይት ሲፈጽሙ የአሜሪካ ዶላር መጠቀም አያስፈልጋቸውም ብለዋል። “እኛ የአሜሪካን ዶላር እየተቃወምን አይደለም፤ በነጻነት ግብይት መፈጸም ስለፈለግን እንጂ” ሲሉም ስለ ዶላር አስፈላጊነት ተናግረዋል። እንደ ኢስት አፍሪካን ጋዜጣ ዘገባ ፕሬዝዳንቱ ሩቶ አክለውም “ዶላር የሚያስፈልገን ከአሜሪካ ጋር ለምናደርገው ግብይት ብቻ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በፈረንጆቹ 1993 የተቋቋመው የአፍሪ ኤክዚም ባንክ ግብይቱ…