07
Aug
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች ዶላር ለመሸጥ ያወጣው ልዩ ጨረታ ውጤትን ይፋ አድርጓል። በዛሬው እለት በተካሄደው ልዩ ጨረታ 27 ባንኮች የሚፈልጉትን የዶላር መጠን እና የሚገዙበትን ዋጋ አስገብተው ተጫርተዋል። ባንኮቹ ለአንድ የአሜሪካ ዶላር ያቀረቡት አማካይ የመግዣ ዋጋ 107.9 ብር መሆኑን ባንኩ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ጨረታው በነገው እለት ባንኮች በሚያወጡት እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ እንዲመጣ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ብሏል ብሔራዊ ባንክ። የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ የዶላር ሽያጭ ጨረታው ውጤትን ሲገልጹ ባለፉት ቀናት በባንኮች እና በብላክ ገበያው መካከል ያለው ልዩነት እየጠበበ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም የውጭ ምንዛሬ መረጋጋትን ያመጣል ያሉት አቶ ማሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሁሉንም የውጭ ምንዛሬ እንቅስቃሴ ወደ ባንክ ስርአት የማስገባት እቅድ…