IGAD

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጃል መሮ ፊት ለፊት ተገናኙ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጃል መሮ ፊት ለፊት ተገናኙ

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራር እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መሪው ጃል መሮ ፊት ለፊት መገናኘታቸው ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመራቸው ተሰምቷል። ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ የሰላም ንግግሩ ጥቂት ቀናትን እንዳስቆጠረና ከሁለቱም ወገኖች የተወጣጡ የጦር አባላት ተወካዮች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው ዛንዚባር የተካሄደውን ድርድር የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ)፣ አሜሪካ፣ ኖርዌይ እና ኬንያ አስተባባሪ እና አሸማጋይ ሚና መውሰዳቸው ይታወሳል። አሁን የተጀመረውን ንግግር ማን እንደሚያደራድር ግልጽ ባይሆንም፣ ኢጋድ ከዚህ ቀደም የነበረውን ሚና ሳያስቀጥል እንዳልቀረ ተጠቅሷል። ከዚህ በተጨማሪ አዲስ…
Read More
አፍሪካ ከዶላር ይልቅ በራሷ ገንዘብ እንድትገበያይ የኬንያ ፕሬዝዳንት ጠየቁ

አፍሪካ ከዶላር ይልቅ በራሷ ገንዘብ እንድትገበያይ የኬንያ ፕሬዝዳንት ጠየቁ

ኬንያ የአፍሪካ ሀገራት የእርስ በርስ ግብይት ሲፈጽሙ እና አገልግሎት ሲለዋወጡ በራሳቸው ገንዘብ ክፍያ  መፈጸም እንዲጀምሩ ጠይቃለች። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ ጅቡቲ ያመሩት የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አፍሪካ በዶላር ላይ ያላት ጥገኝነት ይብቃ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። “ከጂቡቲ እቃ ገዝተን በዶላር የምንከፍለው ለምንድን ነው? ለምን? ምንም ምክንያት የለም”  ያሉት ፕሬዝዳንት ሩቶ ጂቡቲም ሆነች ኬንያ የእርስ በርስ ግብይት ሲፈጽሙ የአሜሪካ ዶላር መጠቀም አያስፈልጋቸውም ብለዋል። “እኛ የአሜሪካን ዶላር እየተቃወምን አይደለም፤ በነጻነት ግብይት መፈጸም ስለፈለግን እንጂ” ሲሉም ስለ ዶላር አስፈላጊነት ተናግረዋል። እንደ ኢስት አፍሪካን ጋዜጣ ዘገባ ፕሬዝዳንቱ ሩቶ አክለውም “ዶላር የሚያስፈልገን ከአሜሪካ ጋር ለምናደርገው ግብይት ብቻ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በፈረንጆቹ 1993 የተቋቋመው የአፍሪ ኤክዚም ባንክ ግብይቱ…
Read More