Conflict

በጋምቤላ በተከሰተ የብሔር ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በጋምቤላ በተከሰተ የብሔር ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በጋምቤላ ክልል በአኙዋክ እና ኑዌር ብሔረሰቦች መካከል በተፈጠረዉ ግጭት እስካሁን ቁጥራቸዉ ከ30 በላይ የሆኑ ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ተናግረዋል። አቶ ኡገቱ ፤ ግጭቱ ግንቦት 13 ላይ አኙዋ እና ሊየር በሰተኙ በሁለት መንደሮች መካከል የተነሳ መሆኑን ገልጸዋል ። ግጭቱ በኋላም ወደ ብሔር ግጭት እየሰፋ የመጣ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊው ግጭቱ በተከሰተበት ወቅትም የክልሉ መንግስት ኮማንድ ፖስት በማቋቋም ከፌዴራል የጸጥታ አካላት ጋር ሁኔታዉን ለማረጋጋት እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። የሟቾች ቁጥር 30 ደርሷል ቢባልም በጸጥታ ግብረ ሀይሉ የተረጋገጠ አይደለም ብለዋል። ሆኖም በግጭቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችል ግን ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በግጭቱ በኢታንግ ልዩ ወረዳ 4…
Read More
በኢትዮጵያ በአንድ ሳምንት ውስጥ 100 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ በአንድ ሳምንት ውስጥ 100 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በአንድ ዓመት ውስጥ ደግሞ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰላም ጥናት ማዕከል አስታውቋል የኢትዮጵያ ፒስ ኢብዘርቫቶሪ የተሰኘው ተቋም ባወጣው ሪፖርት መሰረት በአንድ ሳምንት ውስጥ 100 ኢትዮጵያዊያን ተገድለዋል ብሏል። ከሰኔ 3 ቀን እስከ 9 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተፈጠሩ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት 100 ሰዎች መገደላቸውን የግጭት ሁኔታ መረጃዎችን የሚያቀርበው “ኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቫቶሪ” አስታውቋል። ዓለም አቀፍ የግጭት ሁኔታ እና የክስተት የመረጃ በመሰብሰብና በመተንተን የሚታወቀው “The Armed Conflict Location & Event Data Project” የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ይህንኑ ሥራ በኢትዮጵያ እንዲሠራ በፕሮጀክት ደረጃ ያቋቋመው፣ “Ethiopia Peace Observatory” የተባለው ተቋም ባወጣው ሳምታዊ ሪፖርት፤ በሳምንቱ ከተገደሉት 100…
Read More
በአማራ ክልል ሶስት ዞኖች ጦርነት መጀመሩ ተገለጸ

በአማራ ክልል ሶስት ዞኖች ጦርነት መጀመሩ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው “የሕግ ማስከበር ዘመቻ”ን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። ኮሚሽኑ ይህ ድርጊት በሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን አንድምታና ተጽእኖ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑ አስታውቋል። ኮሚሽኑ አደረኩት ባለው ክትትል በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት አለ ብሏል። በተለይም ሸዋ ሮቢት፣ አርማኒያ፣ አንጾኪያ፣ ገምዛ እና ማጀቴ በመከላከያ ሰራዊት እና በአካባቢው ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥና በከባድ መሣሪያ ጭምር የታገዘ ጥቃት መኖሩን ደርሼበታለሁም ብሏል። በዚህ የተኩስ ልውውጥ ምክንያትም በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ከመድረሱ ባለፈ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ በተለያዩ ጊዜያት መዘጋቱን እንዳረጋገጠ ኮሚሽኑ አስታውቋል። በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተወሰኑ…
Read More
በሰሜን ኢትዮጵያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በሰሜን ኢትዮጵያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም በያዝነው ዓመት ሕዳር ወር የሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል፡፡ ይሁንና የሰላም ስምምነት ቢፈረምም ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ የሕፃናት አድን ድርጅት/ሴቭ ዘ ችልድረን አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ ለኢትዮ ነጋሪ በላከው መግለጫ እንዳለው የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ ያስፈልጋል ብሏል፡፡  በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሕፃናት በላይ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ይህም እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሰ 16 ኢትዮጵያውያን ሕፃናት መሃከል አንዱ ከትምህርት ገበታ መገለሉን ያሳያል ተብሏል፡፡ ይህ አሃዝ ኢትዮጵያን ከትምህርት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቀውስ ካስተናገዱ ሃገራት አንዷ እንደሚያደርጋት ተገልጿል፡፡  በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልል ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በሚገኙ…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 331 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 331 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አደረገች። ለሥራ ጉብኝ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አድርገዋል። አንቶኒ ብሊንከን እንዳስታወቁት ድጋፉ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አማካኝነት የሚሸፈን ነው፡፡ ድጋፉም በተለያዩ ምክንያቶች በችግር ለተጋለጡ ወገኖች ለምግብ፣ ለመድሃኒት፣ ለንጹህ የመጠጥ ውሃ የሚውል መሆኑን ገልፀዋል። ይህም በግጭት ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ፣ በድርቅ ለተጠቁ እና ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ሕይወት አድን ድጋፍ ማድረግ ያስችላል ተብላል።
Read More