07
Aug
መንግሥት፣ ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ሽፋን ይሠጡ የነበሩ ሰባት የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ማገዱን አስታውቋል። ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ ነበሩ የተባሉ 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች ሙሉ በሙሉ መታገዳቸውን የመንግስት ኮሙንኬሽን ሚንስትር እናታለም መለሰ ተናግረዋል። ስማቸው ያልተጠቀሱት እና የታገዱት እነዚህን መተግበሪያዎች በመጠቅም ዜጎች ገንዘባቸውን እንዲበሉ፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዲደረግ ሲያደርጉ እንደነበር ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የትኛውም የምናባዊ መገበያያ መንገዶች መከክልከላቸውን በተደጋጋሚ ሲናገር ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪም መሰረታቸውን በኢትዮጵያ ላደረጉ 36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ አራት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ አመራሮች መታሰራቸውም ተገልጿል። እንዲሁም ምርት ልከው የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ያላደረጉ 29 ላኪ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ…