21
Jun
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ከሓላፊነት ለቀቁ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ዓለም አቀፍ ጨረታ ማሸነፉን ተከትሎ ነበር አንዋር ሶሳ ወደ አዲስ አበባ የመጡት። ከ2019 ጀምሮ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን በስራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩት አንዋር ሶሳ አሁን ላይ ከሀላፊነት መነሳታቸውን ድርጅታቸው አስታውቋል። ይሁንና ሳፋሪኮም ለምን አንዋር ሶሳን ከሀላፊነት እንዳነሳቸው እስካሁን ይፋ አላደረገም። ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአጭር ወራት ውስጥ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን እንዳፈራ አስታውቋል። የኔትወርክ አገልግሎቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም በመከራየት ደንበኞችን እያገለገለ የሚገኘው ሳፋሪ ኮም የኢትዮጵያ ገበያው ያሰበውን ያህል እንዳልሆነለት ከዚህ በፊት መግለጹ አይዘነጋም። ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን መሾሙ ይታወሳል። ላለፉት ሶስት…