Axum

የአክሱም ሀውልት ከሁለት ዓመት ጦርነት በኋላ ለጎብኚዎች ክፍት ተደረገ

የአክሱም ሀውልት ከሁለት ዓመት ጦርነት በኋላ ለጎብኚዎች ክፍት ተደረገ

የአክሱም ሀውልት ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። የጽሕፈት ቤቱ ሀላፊ ገብረመድህን ፍፁም ብርሀን፤ በአክሱም ከተማና አካባቢው የሚገኙ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ጥንታዊ ቅርሶች ለቱሪስቶች ክፍት መደረጋቸውን ተናግረዋል። ቅርሶቹ ዳግም ለጎብኚዎች ክፍት እንዲሆኑ ሕብረተሰቡ በጉልበቱ፣ በገንዘቡና በሙያው ያደረገው ተሳትፎ የላቀ እንደነበርም ገልጸዋል። የቱሪዝሙን ዘርፍ ወደነበረበት ለመመለስና ሕብረተሰቡ ለቱሪስቶች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሳደግ ለፎቶ ግራፍ ባለሙያዎች፣ አስተርጓሚዎች፣ ለባህላዊ ጌጣጌጦችና ቅርፃ ቅርፅ ባለሙያዎች እንዲሁም ለባለ ሆቴሎች ስልጠና መሰጠቱንም አስረድተዋል። በአክሱምና አካባቢው የሚገኙ ቅርሶችና ሙዚየም ለጎብኚዎች ተደራሽ ለማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት መደረጋቸውን ገልጸዋል። በአክሱምና አካባቢው የሚገኙ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ጥንታዊ ቅርሶች ለመጎብኘትና ለማየት በየዓመቱ ከ30 ሺሕ በላይ…
Read More