08
Feb
ጎረቤት ሀገር ሱዳን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ከሚገዙ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ለዓመታት የተጠቀመችበትን እዳ አልከፈለችም ተብሏል፡፡ ሱዳን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተጠቀመችበትን 70 ሚሊዮን ዶላር እዳዋን ባለመክፈሏ ምክንያትም የሚቀርብላት የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን በ50 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡ ካሳለፍነው ሚያዚያ ወር ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ሱዳን ከ8 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ቻድ ደግሞ ሱዳናዊያን የተጠለሉባቸው ሀገራት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ለጎረቤት ሀገራት ከሸጠችው የኤሌክትሪክ ሽያጭ 66 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 47 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የፌደራል ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል። ሱዳን ባለባት የጸጥታ ችግር ምክንያት ከዚህ በፊት የተጠቀመችበትን የኤሌክትሪክ ኃይል ክፍያ በወቅቱ መክፈል አለመቻሏ ለገቢው…