02
Feb
በኢትዮጵያ የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ከተደረገ 17 ዓመት የሆነው ሲሆን የሕዝብ ቁጥሯን በየዓመቱ 10 በመቶ እየጨመረች እየቆጠረች ትገኛለች፡፡ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የጦርነት እና ጸጥታ ችግሮች የሕዝብ ቆጠራውን ለማካሄድ እንቅፋት ሆኖ የቆየ ሲሆን በየጊዜው የፕሮግራም ማራዘም ስታደርግም ነበር፡፡ ከሶት ዓመት በፊት ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ ለማድረግ አራት ቢሊዮን ዶላር በጀት ተመድቦ የባለሙያ እና ቁሳቁስ ዝግጅት የተጀመረ ቢሆንም በሀገሪቱ ባጋጠመ ጦርነት ምክንያት ሳይካሄድ ቆይቷል፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ 4ኛዉ የህዝብ እና ቤት ቆጠራን እስከ 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ለማከናወን ማቀዱን አስታውቋል። ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ይህንን ያስታወቀው ለሶስት ዓመታት በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ስታትስክስ አገልግሎት የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ይፋ ባደረገበት…