ዜና

በኢትዮጵያ ግዙፉ የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ተባለ

በኢትዮጵያ ግዙፉ የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በ5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካ ከሁለት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሥራ እንደሚጀምር ተገልጿል። የከሰል ማዕድን አምራቹ ኢቲ ማይኒንግ ፋብሪካ እንደሚሰኝ ሲገለፅ ፋብሪካው 150 ቶን ከሰል በሰዓት የማምረት አቅምና የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን 75 በመቶ የድንጋይ ከሰል ፍላጎት ለማሟላት ያስችላል ተብሏል። የፋብሪካው ፕሮጀክት ማናጀር ኢንጅነር በላይ አሰፋ የኢትዮጵያ የታጠበ ከሰል ፍላጎት ሀገሪቱ በዓመቱ በአማካይ 400 ሚሊዮን ዶላር እያሳጣት መሆኑን ገልፀዋል። ይህ ፋብሪካ ከሁለት ዓመት በፊት ተጀምሮ በአሁኑ ጊዜ አጠቃላይ ሥራው እየተጠናቀቀ በመሆኑ በፋብሪካው የሚሠሩ ቋሚ ሠራተኞች ሥልጠና እየተሰጠና የሙከራ ሥራዎች ከተሠሩ በኋላ ከሁለት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ተመርቆ ሥራ ይጀምራል ተብሏል።…
Read More
ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

ዋና መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው ስታንዳርድ ባንክ በአፍሪካ ትልቁን ያልተነካ ገበያ እየፈለገ በሚገኝበት በዚህ ጊዜ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሁለት ሳምንት በኃላ የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ ማመልከቻዎችን እንደሚቀበል ከቀናት በፊት መግለፁ አይዘነጋም ። ለዉጪ ፋይናንስ ተቋማት በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንኮች ሆነው እንዲመዘገቡ የቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ ፍቃደኝነቱን በማሳየት "ስታንደርድ ባንክ" ከቀዳሚዎቹ ተርታ መሰለፍ ችሏል። በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ለማግኘት ዝቅተኛው የተከፈለ ካፒታል ለዉጪ ባንኮች 100 ሚሊዮን ብር እና ከባንክ ላልሆኑ የፋይናንስ ተቋማት 25 ሚሊዮን ብር ሀብት ሊኖራቸው ይገባል። ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በባንክ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው የውጭ ባለሀብቶች አምስት የሚደርሱ የባንክ ፈቃድ ለመስጠት ማቀዷን ባሳለፍነው ግንቦት…
Read More
ጣልያን ከኢትዮጵያ የዘረፈቻትን “ፀሀይ” የተሰኘች አውሮፕላንን መለሰች

ጣልያን ከኢትዮጵያ የዘረፈቻትን “ፀሀይ” የተሰኘች አውሮፕላንን መለሰች

በጣልያን-አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ይህችን አውሮፕላን መረከባቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት  "ፀሐይ" አውሮፕላንን ከጣልያን መንግሥት በይፋ መረከባቸውን አስታውቀዋል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ ላለፈው አንድ አመት የአውሮፕላኑን መመለስ ስራ እንዳገዙም ተገልጿል። "ፀሐይ" እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1935 ዓ.ም በጀርመናዊው ኢንጂነር እና የንጉሱ ፓይለት ሄር ሉድዊግ ዌበር ብሎም በወቅቱ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ትብብር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መሰራቷ ይታወሳል። ጣልያን ኢትዮጵያ ቅኝ ለመግዛት ሁለት ጊዜ የሞከረች ቢሆንም የመጀመሪያው ሙከራ በ1880ዎቹ በኢትዮጵያዊያን አርበኞች ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡  በኢትዮጵያዊያን አርበኞች የተባረረችው ጣልያን ሁለተኛውን የቅኝ ግዛት ሙከራዋን በ1927 ያደረገች ሲሆን ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ከአምስት ዓመታት ብርቱ ትግል በኋላ ድል ተቀዳጅተዋል፡፡ ጣልየን በኢትዮጵያ…
Read More
ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ልትከለክል መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ልትከለክል መሆኗን ገለጸች

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር የስድስት ወራት ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ሚኒስትሩ አቶ አለሙ ስሜ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ የሚደረገው ክልከላ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ አቶ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ለፓርላማው እንደተናገሩት፥ ነዳጅ የሚወስዱ ተሽከርካሪዎችን ለግል ጥቅማጥቅ ሆነ ለሌላ አላማ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚደረገውን እገዳ በጥብቅ እንደሚያስፈጽሙ ገልጸዋል። ውሳኔው ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ስጋቶች እና ከባህላዊ የነዳጅ ፍጆታ ጋር ተያይዞ እየጨመረ ለሚመጣው ወጭ ስልታዊ ምላሽ ነውም ተብሏል። እየጨመረ የመጣው የነዳጅ ወጪ ፖሊሲ አውጪዎች አገሪቱ በተለመዱት ተሽከርካሪዎች ላይ ያላትን ጥገኝነት እንዲገመግሙ እና የካርበን በካይ ጋዝ መጠንን ለመቀነስ ከሚደረገው…
Read More
በታሸገ ውሃ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ሊደረግ ነው

በታሸገ ውሃ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ሊደረግ ነው

የታሸገ ውሃ አምራቾች በሦስት ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የታሸገ ውሃ አምራቾች ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ መወሰናቸውን ገልጸዋል። አዲስ በሚጠበቀው የታሸገ ውሃ የማከፋፈያ ዋጋ ጭማሪ በሁለት ሊትር ውሃ ላይ እስከ 20 በመቶ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ይህም በሶት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የውሃ አምራቾቹ በኅዳር ወር በተመሳሳይ የ22.5 በመቶ ጭማሪ አድርገው የነበረ ሲሆን በወቅቱ ለዋጋ ማስተካከያው ምክንያት ነው የተባለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እና ሌሎች ግብአቶች ወጪያቸው ጨምሯል በሚል ነበር። በቀጣይ ሳምንት ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ጭማሪ ምክንያታዊነቱ ላይ ጥያቄ ያስነሳል የተባለ ሲሆን የዋጋ ጭማሪው በተጠቃሚዎች እና አከፋፋዮች ላይ እክል ሊፈጥር እንደሚችል ተገምቷል ሲል…
Read More
የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳይ ሊሰበሰብ ነው

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳይ ሊሰበሰብ ነው

የተባበሩት መንግስታ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያና ሶማሊያ ጉዳይ ላይ ሊሰበሰብ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከአንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል። ስምምነቱን ተከትሎም ሶማሊላንድ የግዛቴ አንድ አካል ናት የምትለው ሶማሊያ የዲፕሎማሲ የበላይነት ለማግኘት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ትገኛለች። በዚሁ መሰረት ሶማሊያ ባለፈው ሳምንት  ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው ስምምነት የተመድን ቻርተር ጥሷል በሚል ምክር ቤቱ ስብሰባ እንዲቀመጥ እና እንዲወያይበት አመልክታም ነበር። ይህንን ተከትሎም የጸጥታው ምክር ቤት የወሩ ፕሬዝዳንት ፈረንሳይ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ጉዳይ ላይ በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት አጀንዳ ስር ለመምከር ስብሰባ መጥራቷ ታውቋል። የጸጥታው ምክር ቤት በዛሬው…
Read More
በአዲስ አበባ በእስረኛ ምግብ ውስጥ ካናቢስ የተሰኘው አደገኛ ዕጽ ተያዘ

በአዲስ አበባ በእስረኛ ምግብ ውስጥ ካናቢስ የተሰኘው አደገኛ ዕጽ ተያዘ

በምግብ ውስጥ  አደንዛዥ ዕፅ  ደብቆ ተጠርጣሪ ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄደው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል። ግለሰቡ ከናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ ይዞ በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ጓደኛውን ለመጠየቅ የሄደው ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ነበር፡፡ ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ጓደኛውን ለመጠየቅ ምግብ ይዞለት የሄደው ይኸው ተጠርጣሪ ከድፍረትም ድፍረት የሚያሰኝ ተግባር ነበር የፈፀመው፡፡ በወቅቱ በሳህን የተቋጠረው ምግብ እንጀራ ፍርፍር በማካሮኒ ነበር፡፡  በእነዚያ የማካሮኒ ቀዳዳዎች ውስጥ የሚያብለጨልጩ ነገሮች ተወታትፈዋል፡፡ ምግቡን ፈትሸው የሚያስገቡት የፖሊስ አባላት ባዩት ነገር ተጠራጥረዋል፤ ምግቡ ተዘርግፎ ሲፈተሽ ብዛት 51 የማካሮኒ ፍሬዎች በተጠቀለሉ የአልሙኒየም ወረቀቶች  አባብጠዋል፡፡ ወረቀቶቹን በመፍታት ለማየት ሲሞከርም ካናቢስ የተባለው አደንዛዥ ዕፅ ሆኖ…
Read More
አቶ ደመቀ መኮንን ከስልጣን ለቀቁ

አቶ ደመቀ መኮንን ከስልጣን ለቀቁ

የኢትዮጵያ ገዢ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ከስልጣናቸው ለቀቁ፡፡  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መሸኘታቸውን ፓርቲያቸው አስታውቋል። የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ " የአመራር የመተካካት መርኅን እና የአሠራር ሥርዓት በመከተል አቶ ደመቀን በክብር ተሸኝተዋል " ሲል ገልጿል። አቶ ደመቀን መኮንንን በመተካት የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። አቶ ደመቀ ከፓርቲው አመራርነታቸው መሰናበት በአገሪቱን መንግሥት ውስጥ ይዘው ከሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን ሊለቁ እንደሚችሉ አመላካች መሆኑ ተነግሯል። አቶ ደመቀ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነትና…
Read More
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።

የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።

የደቡብ አሜሪካዋ ብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ አፍሪካ እንደሚመጡ ተገልጻል። እንደ ብራዚል ዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ አዲስ አዲስ አበባ ይመጣሉ። ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ በአዲስ አበባ ቆይታቸው በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉም ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ ከአዲስ አበባ በተጨማሪም በግብጽ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ተገልጿል። ከአፍሪካ በመቀጠል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጥቁር ህዝቦች የሚኖሩባት ብራዚል ከአፍሪካ ጋር የሚያስተሳስራት ብዙ ታሪክ አላት። ፕሬዝዳንቱ ዳ ሲልቫ ስለ ጉብኝታቸው እንዳሉት "ብራዚል ከአፍሪካ ጋር ያለባትን የታሪክ እዳ መክፈል ትፈልጋለች" ብለዋል። ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አፍሪካ የሚጓዙት ፕሬዝዳንት ሲልቫ ከዚህ በፊት በአንጎላ፣ ኬፕ ቩርዴ እንዲሁም በሳኦቶሜ…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት  11 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት  11 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወይዘሪት ፍሬህይወት የ2016 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡ ተቋሙ በስድስት ወሩ በመላው ሀገሪቱ 232 አዳዲስ የሞባይል  ኔትወርክ ጣቢያዎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል ብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ተጨማሪ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን  አዲስ የሞባይል  ኔትወርክ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል መሰረተ ልማት መገንባቱን የገለጸ ሲሆን የድርጅቱ አጠቃይ ደንበኞች ቁጥርም 81 ሚሊዮን እንደደረሱ ተገልጿል፡፡ እንዲሁም በግማሽ ዓመቱ ውስጥ በገጠራማ የሀገሪቱ አካባቢዎች 41 አዲስ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋልም ተብሏል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌኮም ደንበኞች ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛው ተቋም ሲሆን ከሶስት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ለገባው ሳፋሪኮም የቴሌኮም ኩባንያ ጋር ብርቱ ፉክክር እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ ድርጅቱ ባለፉት…
Read More