piassa

የአዲስ አበባ እምብርት ከምትባለው ፒያሳ 11 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ከንቲባ አዳነች ተናገሩ

የአዲስ አበባ እምብርት ከምትባለው ፒያሳ 11 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ከንቲባ አዳነች ተናገሩ

በአዲስ አበባ ከፒያሳ እና አካባቢው ከሳምንታት በፊት በተጀመረው የከተማ ማስዋብ ግንባታ ምክንያት 11 ሺህ ሰዎች መነሳታቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል። ከንቲባዋ በሁሉም የመንግስት ሚዲያዎች በተላለፈ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት “በድምሩ ወደ 11 ሺህ ሰው ይሆናል ከዚያ አካባቢ ወደተሻለ ቦታ የወሰድነው” ብለዋል። ነዋሪዎቹ መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰው በፒያሳ አካባቢ ካሉት ራስ መኮንን ድልድይ፣ ማህሙድ ሙዚቃ ቤት፣ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ፣ አራት ኪሎ የሚገኘው አብርሆት ቤተ መጽሐፍት፣ ቴዎድሮስ አደባባይ እስከ ቸርችል ጎዳና ድረስ በሚያካልለው “የኮሪደር ልማት” ምክንያት የተነሱ ናቸው። ይህ የኮሪደር ልማት ከፒያሳ እስከ አራት ኪሎ ባለው አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ 8.1 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ከንቲባዋ ገልጸዋል። አዳነች በዚህ ሪፖርት ላይ ከተነሺዎቹ…
Read More