ዜና

ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀገሯ እንዳይበር አገደች

ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀገሯ እንዳይበር አገደች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ከመስከረም ወር ጀምሮ አየር መንገዳችን ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን ሁሉንም በረራ ማገዱን አሳውቆናል” ብሏል፡፡ ኤርትራ የትራንስፖርት እና ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስቴር የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀጣዩ መስከረም በኋላ ወደ አሥመራ እንዳይበር ማገዱን የሚያሳውቅ ማስታወቂያ በዛሬው እለት አውጥቷል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን አስመለክቱ በሰጠው መግለጫ፤ “የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ሐምሌ 14 2016 ዓ.ም ወይም በፈረንጆቹ 21 ጁላይ 2024 በላከው ደብዳቤ በፈረንጆቹ ከመስከረም 30 ቀን 2024 ዓ.ም. ጀምሮ አየር መንገዳችን ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን ሁሉንም በረራ ማገዱን አሳውቆናል” ብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳዩን አስመልክቶ የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ጉዳዩም በበጎ መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ያለውን…
Read More
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ተመረጠ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ተመረጠ

የአሜሪካው አለምአቀፍ የስፓርት ቻናል (ኢኤስፒኤን) ቀነኒሳ በቀለን የ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ አትሌት ነው ሲል መርጦታል፡፡ የስፖርት ቻናሉ ከቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ ሌላኛዋ ኢትዮጵያት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ በ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ ያላቸውን የአፍሪካ ስፓርተኞች ይፋ አድርጓል። ኢኤስፒኤን አህጉሪቱ ካላት ስፋት እና የስፖርት ብዛት አንጻር 25 ምርጥ አትሌቶችን መምረጥ ከባድ መሆኑን አስታውቋል። ዓለም ካየቻቸው ምርጥ የማራቶን ሯጭ አንዱ ከሆነው ኢሉድ ኪፕቾጌ እና ኦሎምፒክ እና በርካታ የአውሮፓ ሻሜፒዮን ሽፕ አሸናፊ ከሆነው ሳሙኤል ኢቶ ማንን ትመርጣላችሁ? ሲልም ኢኤስፒኤን ይጠይቃል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቻናሉ ዘገባ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ስሙ በመካተቱ እንደተደሰተ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ ጽፏል። አትሌት ቀነኒሳ በ2000ዎቹ በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር…
Read More
አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ቦብ ሜንድዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋገጠ

አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ቦብ ሜንድዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋገጠ

ቦብ ሜንድዝ ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ የሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ የዘር ሀረጋቸው ከኩባ የሚመዘዘው ሜንድዝ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤትን ከመቀላቀላቸው በፊት የኒው ጀርሲዋን ዩኒየን ሲቲን በከንቲባነት አገልግለዋል፡፡ እኝህ ጉምቱ ፖለቲከኛ በፈረንጆቹ 2020 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አድርገዋል ተብሏል፡፡ እንደ አሜሪካ ድምጽ ዘገባ ከሆነ ፖለቲከኛው ይህን ያደረጉት ከግብጽ ባለስልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጉቦ ከተቀበሉ በኋላ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ…
Read More
የፓሪስ ክለብ እና ቻይና ኢትዮጵያ አዲስ ብድር እንድታገኝ ፈቀዱ

የፓሪስ ክለብ እና ቻይና ኢትዮጵያ አዲስ ብድር እንድታገኝ ፈቀዱ

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ ሊሰጠው ያሰበውን ብድር እና እርዳታ የከለከለው፡፡ ጦርነቱ እንዲቆም ያደረገው የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የቆመውን ጨምሮ አዲስ ብድር እንዲሰጣት ለተቋሙ ጥያቄ ያቀረበች ቢሆንም በተደጋጋሚ የተደረጉ ውይይቶች የታሰበውን ያህል ፍሬ ሳያፈሩ ቆይተዋል፡፡ አይኤምኤፍ በድር ለኢትዮጵያ ከመፍቀዱ በፊት 20 አባላት ያሉት ፓሪስ ክለብ በመባል የሚጠራው የበለጸጉ ሀገራት ስብስብ ብድር እንዲሰጥ ይሁንታ እንዲሰጥ ሲጠበቅ ነበር፡፡ የሀገራትን ብድር የመክፈል አቅም በመገምገም ውሳኔ የሚሰጠው ይህ ስብስብ የኢትዮጵያንም አቅም ሲገመግም ቆይቶ ለአይኤምኤፍ ፈቃድ እንደሰጠ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ ከፓሪስ ክለብ በተጨማሪም ሌላኛዋ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ብድር የሰጠችው ቻይና ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ተጨማሪ ብድር እንዲሰጣት ይሁንታቸውንን ሰጥተዋልም…
Read More
የኢትዮጵያ ውጪ ንግድ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

የኢትዮጵያ ውጪ ንግድ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳ ነበር፡፡ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቋል፡፡ የተገኘው ገቢ ባለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው 3 ነጥብ 64 ቢሊየን ዶላር የ4.6 በመቶ ወይም በ166 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው፡፡ ከተገኘው ገቢ የግብርናው ዘርፍ 76 በመቶ በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ሲሆን ማኑፋክቸሪንግ ማእድን ፣ኤሌክትሪክና ሌሎች በተከታታይ የሚገኙ ናቸው። ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከ3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ከውጭ ሀገራት ግዢ በመፈጸም ለተጠቃሚዎች እንደተሰራጨም ተገልጿል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን…
Read More
ኢትዮጵያ የመንግስት ተቋማት አመራሮች ተጨማሪ ገቢ እንዳያገኙ የሚከለክል ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ የመንግስት ተቋማት አመራሮች ተጨማሪ ገቢ እንዳያገኙ የሚከለክል ህግ አዘጋጀች

የመንግስት አመራሮች ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ ስራን መስራት እንዳይችሉ የሚደነግግ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጀ፡፡ የፌደራል የስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዳስታወቀው ማንኛውም የመንግስት አመራር ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ ንግድ እና መስል ስራዎችን መስራት የሚከለክል ረቂቅ ደንብ መዘጋጀቱን አስታውቋል። የመንግስት አመራሮች ለሙስና ተጋላጭ ናቸው ተብለው ከተለዩ ዘርፎች ውስጥ መሆናቸው የሚናገሩት የኮሚሽኑ የሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን በላይነህ በህዝብ ሃብት ላይ ውሳኔን የሚያሳልፉ አካላት የመንግስትና የህዝብን ስራ ብቻ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽኑ ለከፍተኛ ባለስልጣናት የጥቅም ግጭት መከላከል እና የሥነ-ምግባር ደንብ ረቂቅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መላኩን የሚናገሩት ሥራ አስፈፃሚው፤ አመራሮች ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን ሲሰሩ የጥቅም ግጭቶች እንደሚከሰቱ እና አግባብ ባልሆነ መንገድ…
Read More
ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በፓርላማ በማጽደቅ ስድስተኛ ሀገር ሆናለች፡፡ የናይል ተፋሰስ አባል የሆኑ 11 ሀገራት በኡጋንዳ ኢንተቤ ባደረጉት ስምምነት የናይል ወንዝን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ ስምምነት ነው፡፡ ስምምነቱ ከ11 የናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ስድስት ሀገራት በፓርላማ ካጸደቁ ቋሚ የናይል ተፋሰስ ሀገራት ኮሚሽን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ መግባት ይችላል ተብሏል፡፡ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ እንደገለጹት የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል ከተፈረመ ቆይቷል፡፡ አምስት ሀገራት በፓርላማቸው አጽድቀው ነበር፡፡ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ለመመስረት የሚጠበቀው ስድስተኛ ሀገር በፓርላማ እስኪያጸድቅ ድረስ ነበር፤ ደቡብ ሱዳን አጸድቃለች ብለዋል፡፡ ስድስት ሀገራት የናይል ስምምነት ማዕቀፍን ማጽደቃቸው ፋይዳው ከፍተኛ ነው ያሉት አምባሳደሩ…
Read More
ኢትዮጵያ H5170 በሚል ስያሜ ለጡት ካንሰር ታማሚዎች የሚሰጠውን መድሃኒት እንዳይጠቀሙ አሳሰበች፡፡

ኢትዮጵያ H5170 በሚል ስያሜ ለጡት ካንሰር ታማሚዎች የሚሰጠውን መድሃኒት እንዳይጠቀሙ አሳሰበች፡፡

ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ ከሆፍማን ሮቼ ኢትድ የንግድ ተወካይ ጽህፈት ቤት የተላከውን ማስታወቂያ እና በኬኒያ ፒፒቢ የተሰራጨውን የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያ ዋቢ ማድረጉን ገልጿል። በዚህ መሠረት ባለሥልጣኑ በጥያቄ ውስጥ ያሉትን ምርቶች የገበያ ፈቃድ በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ግምገማ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ሄርሴፕቲን 440 ሚ.ግ  ወደ  ኢትዮጵያ ለገበያ ለማቅረብ የተመዘገበ ተመዝግቧል ብሏል፡፡ መድሃኒቱ የምርት ስሙ ሄርሴፕቲን 440 ሚሊግራም የሆነ፣ ጄንቴክ ኢንክ በተባለ አምራች ኩባንያ በአሜሪካ የተመረተ፣ የፈቃድ ባለቤት ኤፍ ሆፍማን ላ ሮቼ የተሰራበት መንገድ ደግሞ ፓውደር የሆነ በመርፌ መልክ የሚሰጥ ነውም ተብሏል፡፡ እንዲሁም መድሃኒቱ የባች ቁጥር 05830083 የሆነ በኬኒያ ሀሰተኛ መድኃኒት መሆኑን የተረጋገጠና ከኢትዮጵያ በባች ቁጥር H5170 በሚል የተረጋገጠ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡ የመድኃኒቱ ምርት በተፈቀደላቸው አስመጪዎችና…
Read More
ሐገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከክልሎች የምክክር አጀንዳ ሊያሰባስብ መሆኑን አስታወቀ

ሐገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከክልሎች የምክክር አጀንዳ ሊያሰባስብ መሆኑን አስታወቀ

ኮሚሽኑ በክልሎች የሚያደርገውን የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ስራ በመጪው ሳምንት እንደሚጀምር አስታውቋል። አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ድሬዳዋ ከተማ አሰተዳደርን ጨምሮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ እና በሀረሪ ክልሎች እንደሚካሄድም ነው ያስታወቀው ኮሚሽኑ። ሂደቱን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ዘገየ አስፋው አጀንዳ በማሰባሰብ ስራው የሚሳተፉ ተወካዮች መረጣ አስቀድሞ በመጠናቀቁ ስራው ድሬዳዋን ጨምሮ በሶስቱ ክልሎች ይካሄዳል ብለዋል። ከሳምንት በኋላ ቀደም ሲል በተጠቀሱት ሶስት ክልሎች ይካሄዳል የተባለው አጀንዳ የማሰባሰብ ስራ ከአዲስ አበባው ጋር ተመሳሳይ በሆነ ሂደት እንደሚፈጸምም ነው ኮሚሽነር ዘገየ የተናገሩት። በየክልሉ ካሉ 10 የህብረተሰብ ክፍሎች የተመረጡ የወረዳ ተወካዮች ወደ ክልል ከተሞቹ እንዲመጡ ከተደረገ በኋላ ተመካክረው አጀንዳዎቻቸውን እንዲለዩና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር እንዲመካከሩ ይደረጋል…
Read More
ኢትዮጵያ በየዓመቱ 100 ሺህ ሔክታር መሬት በአዲስ የቡና ዝርያ እየተካች መሆኗ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በየዓመቱ 100 ሺህ ሔክታር መሬት በአዲስ የቡና ዝርያ እየተካች መሆኗ ተገለጸ

የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ላይ ባደረሱት ጥቃት የኢትዮጵያ ቡና ንግድ ለሶስት ቀናት ተስተጓጉሎ እንደነበር ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት የውጪ ንግድ አፈጻጸም ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንዳሉት ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት ውስጥ 350 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር ብለዋል፡፡ ይሁንና አፈጻጸሙ 298 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ሀገራት የምትልከው ቡና በቀይ ባህር በኩል በመሆኑ እና የሀውቲ ታጣቂዎች በሚያደርሱት ጥቃት ምክንያት መስጓጎል ገጥሞት እንደነበርም ተገልጿል፡፡ እንደ ዋና…
Read More