22
Jul
የአሜሪካው አለምአቀፍ የስፓርት ቻናል (ኢኤስፒኤን) ቀነኒሳ በቀለን የ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ አትሌት ነው ሲል መርጦታል፡፡ የስፖርት ቻናሉ ከቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ ሌላኛዋ ኢትዮጵያት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ በ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ ያላቸውን የአፍሪካ ስፓርተኞች ይፋ አድርጓል። ኢኤስፒኤን አህጉሪቱ ካላት ስፋት እና የስፖርት ብዛት አንጻር 25 ምርጥ አትሌቶችን መምረጥ ከባድ መሆኑን አስታውቋል። ዓለም ካየቻቸው ምርጥ የማራቶን ሯጭ አንዱ ከሆነው ኢሉድ ኪፕቾጌ እና ኦሎምፒክ እና በርካታ የአውሮፓ ሻሜፒዮን ሽፕ አሸናፊ ከሆነው ሳሙኤል ኢቶ ማንን ትመርጣላችሁ? ሲልም ኢኤስፒኤን ይጠይቃል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቻናሉ ዘገባ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ስሙ በመካተቱ እንደተደሰተ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ ጽፏል። አትሌት ቀነኒሳ በ2000ዎቹ በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር…