ዜና

ኢትዮጵያ በሊባኖስ የሚኖሩ ዜጎቿን አስጠነቀቀች

ኢትዮጵያ በሊባኖስ የሚኖሩ ዜጎቿን አስጠነቀቀች

በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል። እስራኤል የሃመስ መሪ ኢስማኤል ሃኒየህ እና የሊባሱ ሄዝቦላህ የጦር መሪ ፉአድ ችኩር መግደሏን ተከትሎ ኢራን በእስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች። የኢራንን ዛቻ ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ከፍተኛ ስጋት በመንገሱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረጉ በረራዎች የተሰረዙ ሲሆን ሀገራትም ዜጎቻቸውን በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው። በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ የቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፤ በሊባኖስ እና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ስጋት እና ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መምጣቱን አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ለማስጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በትኩረት እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና…
Read More
የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀት 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ደረሰ

የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀት 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ደረሰ

መንግስት 550 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አዘጋጅቷል ከሁለት ወር በፊት 970 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አጽድቆ የነበረው የፌደራል መንግስት ግማሽ ትሪሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዳሉት የፌደራል መንግሥት 551 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ  ተናግረዋል። መንገስት ካቀረበው 550 ቢሊዮን ብር ውስጥ 240 ቢሊዮን ብሩ "ለማኅበራዊ ድጋፍ " የሚውል ነው የተባለ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ለማህበራዊ ድጋፍ፣ ለምግብ ዋስትና፣ ለሰራተኛ ደመወዝ ጭማሪ፣ ለመድሃኒት ድጎማ፣ ለለነዳጅ ድጎማ እና ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች ድጎማ እንደሚውል ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ የፌደራል መንግስት የበጀት ማስተካከያ ያደረገው ከዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ የገንዘብ ድጋፍ በብድር እና እርዳታ ማግኘቱን ተከትሎ ነው፡፡…
Read More
ራይላ ኦዲንጋ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ለመሆን እጩ ሆነው ተመዘገቡ

ራይላ ኦዲንጋ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ለመሆን እጩ ሆነው ተመዘገቡ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ምርጫ በየአራት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት የህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሃማት ስልጣን ሊጠናቀቅ አንድ ዓመት ብቻ ቀርቶታል፡፡ ይህን ተከትሎም ህብረቱ ማስታወቂያ ያወጣ ሲሆን የኬንያ ፕሬዝዳንት ለመሆን አራት ጊዜ ተወዳድረው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በይፋ ጥያቄ አቀርበዋል፡፡ የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የራይላ ኦዲንጋ ጥያቄን በአዲስ አበባ በይፋ ለአፍሪካ ህብረት አቅርቧል፡፡ የአፍሪካ ህብረት እጩ ተወዳዳሪዎች እንዲመዘገቡ ያስቀመጠው ጊዜ የፊታችን ማክሰኞ የሚያበቃ ሲሆን ኬንያ ራይላ ኦዲንጋን ዋነኛ እጩ አድርጋ አስመዘግባለች፡፡ ከኬንያ በተጨማሪ ጅቡቲ፣ ሲሸልስ እና ሶማሊያም እጩ ያስመዘገቡ ሲሆን ራይላ ኦዲንጋ የተሻለ ድምጽ ሊያገኙ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ እጩዎች ከተመዘገቡ በኋላ ኢትዮጵያዊቷ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጅት ስነጊዮርጊስ አባል የሆኑት የአፍሪካ…
Read More
ኢትዮጵያ ዜጎቿ ወደ ታይላንድ እና ማይናማር እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

ኢትዮጵያ ዜጎቿ ወደ ታይላንድ እና ማይናማር እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

ኢትዮጵያ ከታይላንድ እና ማይናማር ጋር ምንም አይነት የስራ ስምምነት እንደሌላት ገልጻለች የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ላይ እንዳሉት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ወደ እስያዎቹ ታይላንድ እና ማይናማር በህገወጥ ደላሎች እየተታለሉ እየተጓዙ መሆኑን ተናግረዋል ። ኢትዮጵያዊያኑ ለስራ በሚል ወደ ሁለቱ ሀገራት እየተጓዙ መሆኑን አውቀናል ያሉት አምባሳደር ነብዩ ይሁንና ኢትዮጵያ ከተባሉት ሀገራት ጋር የስራ ስምምነት እንዳልተፈራረመች ተናግረዋል። በህገወጥ ደላሎች ተታለው ወደ ስፍራው የሄዱ እና በጉዳት ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳትም በቶኪዮ እና ኒው ዴልሒ ባሉ ኢምባሲዎች በኩል ጥረቶች በመደረግ ላይ እንደሆነ አምባሳደር ነብዩ ገልጸዋል። አምባሳደር ነብዩ በመግለጫቸው ላይ ያነሱት ሌላኛው ጉዳይ የኢትዮጵያ እና…
Read More
ጸረ ሙስና ኮሚሽን የ113 አመራሮችን ሃብት እያጣራ መሆኑን አስታወቀ

ጸረ ሙስና ኮሚሽን የ113 አመራሮችን ሃብት እያጣራ መሆኑን አስታወቀ

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2016 በጀት አመት ሃብታቸውን ካስመዘገቡት አመራሮች መካከል በተጨማሪም የሃብት ማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ በአንድ መቶ አስራ ሦስት ውሳኔ ሰጪ አመራሮች ላይ የሃብት ማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑን የኮሚሽኑ የሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን በላይነህ ተናረዋል፡፡ ያስመዘገቡት ሃብት አጠራጣሪ ሁኖ በተገኙና በተደረጉ ጥቆማዎች መሰረት በውሳኔ ሰጪ አመራሮች ላይ የሃብት ማጣራት ሥራ እየተሰራ እንዳለ ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡ ኮሚሽኑ በሚሰራው የሃብት ማጣራት ሥራ ሃታቸው ለሙስና የተጋለጡትን ለፍትህ ሚኒስቴር እንደሚሳውቅም ጠቁመዋል፡፡ ሃብታቸው እየተጣራ ያሉትን ውሳኔ ሰጪ አመራሮች በአሁኑ ሰዓት ይፋ ማድርጉ ያልተመዘገቡ ሃብቶችን እንዲያሸሹ ስለሚያደርግ ከማጣራት ሥራው በኋላ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ ከህብረተሰቡ ጋር በይበልጥ…
Read More
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ሰጠ

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ሰጠ

የዓለም ባንክ የዳይሬክቶች ቦርድ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለኢትዮጵያ የ16 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ብድር እና እርዳታ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ የዓለም ባንክ በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫው የገንዘብ ድጋፍና ብድሩ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለመደገፍ የሚውል መሆኑን አስታውቋል። በዚህ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ድጋፍ መሆኑን የገለጸው ባንኩ፤ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ የተራዘመ ብድር ነው ብሏል። የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለችውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችንም ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት 1 ቢሊዮን ዶላር የቀጥታ እርዳታ ሲሆን 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ ማራዘሚያ እንዲሁም 320 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር በሚል…
Read More
ኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘቧን በ31 በመቶ አዳከመች

ኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘቧን በ31 በመቶ አዳከመች

ኢትዮጵያ ከዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ ማድረግ ጀምራለች፡፡ ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በዲሱን የምንዛሬ ተመን ዛሬ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ማሻሻውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫው የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወስንበት የገበያ ሥርዓት መሸጋገሩን አስታውቋል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ74.7364 ብር እየተገዛ በ76.2311 እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል። ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ የ18 ብር ጭማሪ ታይቷል። በኢትዮጵያ ንግድ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ቢሊዮን ዶላር አተረፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ቢሊዮን ዶላር አተረፈ

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ 7 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሰጠው መግለጫ በተያዘው በጀት ዓመት 7.02 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል። የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ ይህ ትርፍ ከባለፈው ከመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል። ትርፉ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ 402 ቢሊዮን ብር እንደሚሆን ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። ስራ አስፈጻሚው እንደገለጹት አየርመንገዱ 577,746 የበረራ ሰአቶችን ማስመዝገቡን እና ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ19 በመቶ ጭማሪ አለው።  በበጀት አመቱ 17.1 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገዱን የገለጸው አየር መንገዱ ከእነዚህ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆኑት አለምአቀፍ መንገደኞች ሲሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑን ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ናቸው ብሏል።…
Read More
በጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለ

በጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን በደረሰው ተከታታይ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ያገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ ባወጣው የሁኔታዎች መግለጫ ላይ በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል አመልክቷል። እሁድ ሐምሌ 14 እና ሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ተቀብረው የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ዛሬም ለአራተኛ ቀን እየተካሄደ ነው። በአደጋው ስፍራ ዛሬን ጨምሮ በአካባቢው እየጣለ ባለው ዝናብ ውስጥ ጭምር ከተንሸራተተው መሬት ስር ለማውጣት የሚደረገው የነፍስ አድን ጥረት ቀጥሏል።…
Read More
በኢትዮጵያ በመሬት መንሸራተት አደጋ ከ260 በላይ ዜጎች ሞቱ

በኢትዮጵያ በመሬት መንሸራተት አደጋ ከ260 በላይ ዜጎች ሞቱ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ከትናንት በስቲያ በደረሰ የመሬት ናዳ አደጋ የሞቱ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን እስከ ትንናት ምሽት ድረስ የሟቾች ቁጥር 229 ነበር። የገዜ ጎፋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ የሟቾች ቁጥር ወደ 260 ማሻቀቡን ተናግረዋል። እስካሁን በተደረገው ፍለጋ ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ በድምሩ የ260 ሰዎች አስክሬን የተገኘ ሲሆን፣ የአስክሬን ፍለጋ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችልና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን  ተናግረዋል። አደጋው መጀመሪያ ሶስት ቤተሰብ ላይ…
Read More