02
Aug
ኢትዮጵያ ከታይላንድ እና ማይናማር ጋር ምንም አይነት የስራ ስምምነት እንደሌላት ገልጻለች የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ላይ እንዳሉት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ወደ እስያዎቹ ታይላንድ እና ማይናማር በህገወጥ ደላሎች እየተታለሉ እየተጓዙ መሆኑን ተናግረዋል ። ኢትዮጵያዊያኑ ለስራ በሚል ወደ ሁለቱ ሀገራት እየተጓዙ መሆኑን አውቀናል ያሉት አምባሳደር ነብዩ ይሁንና ኢትዮጵያ ከተባሉት ሀገራት ጋር የስራ ስምምነት እንዳልተፈራረመች ተናግረዋል። በህገወጥ ደላሎች ተታለው ወደ ስፍራው የሄዱ እና በጉዳት ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳትም በቶኪዮ እና ኒው ዴልሒ ባሉ ኢምባሲዎች በኩል ጥረቶች በመደረግ ላይ እንደሆነ አምባሳደር ነብዩ ገልጸዋል። አምባሳደር ነብዩ በመግለጫቸው ላይ ያነሱት ሌላኛው ጉዳይ የኢትዮጵያ እና…