Gofalandslide

በጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለ

በጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን በደረሰው ተከታታይ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ያገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ ባወጣው የሁኔታዎች መግለጫ ላይ በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል አመልክቷል። እሁድ ሐምሌ 14 እና ሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ተቀብረው የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ዛሬም ለአራተኛ ቀን እየተካሄደ ነው። በአደጋው ስፍራ ዛሬን ጨምሮ በአካባቢው እየጣለ ባለው ዝናብ ውስጥ ጭምር ከተንሸራተተው መሬት ስር ለማውጣት የሚደረገው የነፍስ አድን ጥረት ቀጥሏል።…
Read More
በኢትዮጵያ በመሬት መንሸራተት አደጋ ከ260 በላይ ዜጎች ሞቱ

በኢትዮጵያ በመሬት መንሸራተት አደጋ ከ260 በላይ ዜጎች ሞቱ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ከትናንት በስቲያ በደረሰ የመሬት ናዳ አደጋ የሞቱ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን እስከ ትንናት ምሽት ድረስ የሟቾች ቁጥር 229 ነበር። የገዜ ጎፋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ የሟቾች ቁጥር ወደ 260 ማሻቀቡን ተናግረዋል። እስካሁን በተደረገው ፍለጋ ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ በድምሩ የ260 ሰዎች አስክሬን የተገኘ ሲሆን፣ የአስክሬን ፍለጋ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችልና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን  ተናግረዋል። አደጋው መጀመሪያ ሶስት ቤተሰብ ላይ…
Read More