መነሻ ገፅ

​ሳዑዲ ዓረቢያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ድንበር ሲያቋርጡ ማሰሯን ገለጸች

​ሳዑዲ ዓረቢያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ድንበር ሲያቋርጡ ማሰሯን ገለጸች

አንደ ገልፍ ኒውስ ዘገባ የድንበር ጠባቂዎች ባለፉት አንድ ሳምንት ውስጥ 1,924 ሰዎች ሳዑዲ ዓረቢያ ለመግባት ሲሞክሩ በሕገ-ወጥ መንገድ ተይዘዋል ብለዋል። ከእነዚህ ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን፣ 37 በመቶ የመን እና ቀሪዎቹ ደግሞ የሌሎች አገሮች ዜጎች ናቸው። በተጨማሪም 32 ሰዎች ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ ተይዘዋል። ​በዘመቻው ወቅት ሕገ-ወጥ ስደተኞችን በትራንስፖርት፣ በመጠለያ ወይም በቅጥር ሥራ በማገዝ የተጠረጠሩ ተጨማሪ 31 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ​በአሁኑ ወቅት 30,236 የውጭ አገር ዜጎች የሕግ ሂደቶች እስኪጠናቀቁ ድረስ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ። ​የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ማጓጓዝ፣ ማኖር ወይም በምንም መንገድ መርዳት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት፣ እስከ 1 ሚሊዮን ሪያል በሚደርስ ቅጣት እና ጥቅም…
Read More
ኢትዮጵያ የኤርትራ ፖሊሲዬ “ሙሉ በሙሉ ከሸፈ” አለች

ኢትዮጵያ የኤርትራ ፖሊሲዬ “ሙሉ በሙሉ ከሸፈ” አለች

ከኤርትራ ጋር በትብብር ላይ የተመሰረተ፣ አዎንታዊ እና ገንቢ የረጅም ጊዜ ግንኙነትን ለመመስረት የሚያስችል አካሄድን ወይም ፖሊሲን ስንከተል ነበር ያሉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፖሊሲው አሁን "ሙሉ በሙሉ ከሽፏል" ብለዋል። ለፖሊሲው መክሸፍ "አጋጣሚውን መጠቀም አልተቻለም" ያሉትን የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን የኤርትራ አገዛዝ ተጠያቂ አድርገዋል። አገዛዙ በኢትዮጵያ ላይ እየተከተለ ባለው 'የተሳሳተ' ፖሊሲ ምክንያት ዘላቂ ግንኙነት ለመመስረት የተደረጉ ሙከራዎች ሁሉ ሙሉ በሙሉ መክሸፋቸውንም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ትኩረቱን በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ባሉ ወቅታዊ የፖለቲካና የደህንነት ሁነቶች ላይአድርጎ ትናንት ሐሙስ ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ የተናገሩት። በመድረኩ ሁነቶችን…
Read More
ኢትዮጵያ የውጭ ዜጎችን ጨምሮ ከ112 ዜጎችን ከክሪፕቶ ግብይት ጋር በተያያዘ አሰረች

ኢትዮጵያ የውጭ ዜጎችን ጨምሮ ከ112 ዜጎችን ከክሪፕቶ ግብይት ጋር በተያያዘ አሰረች

በክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያዎች ጭምር በመታገዝ ህገ ወጥ የምንዛሬ ዝውውር ያደርጉ ነበር የተባሉ ቻይናውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ በተቀናጀ መንገድ ሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮችን ሲፈጽሙ ደረስኩባቸው ያላቸውን 112 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ያስታወቀው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት 8 ቻይናውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ለመንግሥት ብዙሀን መገናኛዎች በላከው መግለጫ ይፋ አድርጓል። በመግለጫው በተደራጀ መንገድ በስውር ሲፈጸም ነበር ያለውን ህገ ወጥ የምንዛሬ ገንዘብ ዝውውርና አሻጥር ለማምከን የሚያስችል ምስጢራዊ የመረጃ ስምሪቶችን ሲያደርግ እንደቆየ ያስታወቀው አገልግሎቱ ቻይናውያኑን ጨምሮ 112 ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች   በቁጥጥር  ሥር  መዋላቸውን፤ ከሕገ - ወጥ ተግባሩ ጋር ትስስር የነበራቸው አምስት መቶ አስራ ዘጠኝ የባንክ አካውንቶች መታገዳቸውን እንዲሁም የተለያዩ ኤግዚቢቶች መያዛቸውን…
Read More
ኢትዮጵያ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎቿን ከውጭ ሀገራት መመለሷን ገለጸች

ኢትዮጵያ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎቿን ከውጭ ሀገራት መመለሷን ገለጸች

ከመስከረም ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ከ17 ሺሕ በላይ ዜጎች ወደ ሀገር መመለሳቸው ተገልጿል። በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ዜጎችን ከ17 ሺሕ በላይ ዜጎችን ከመስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተሰራ ሥራ መመለስ መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡ "ከውጭ ግንኙነት ቁልፍ ሥራዎች አንዱ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ነው" ያለው ሚኒስቴሩ ፖሊሲውን በአግባቡ ለመተግበር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎችን መብት ማስከበር፣ ለዜጎች ተገቢ የቆንስላ አገልግሎት መስጠት፣ በሄዱበት ሀገር ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውና የሀገሩ መንግሥት ዜጎቻችን ሀገራቸውን እንዲለቁ ሲወስን መብታቸው፣ ክብራቸውና…
Read More
በኢትዮጵያ ታግቶ የነበረው ኬንያዊ ዜጋ መለቀቁ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ታግቶ የነበረው ኬንያዊ ዜጋ መለቀቁ ተገለጸ

በኢትዮጵያ በአጋቾች ታግቶ የቆየው ኬንያዊ ዜጋ 3 ሚሊየን ሽልንግ ከተከፈለ በኋላ መለቀቁን ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ። የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር እና በአዲስ አበባ ያሉት አምባሳደራቸው ባደረጉት ጥረት 3 ሚሊየን የኬንያ ሽልንግ ለአጋቾች ከተከፈለ በኋላ ሳሙኤል ንጃጊ የተባለው ዜጋቸው መለቀቁን ገልፀዋል። ሳሙኤል ከሳምንት በፊት በደብረ ብርሃን ከተማ ተቀጥሮ ከሚሰራበት ድርጅት ታግቶ የተወሰደ ሲሆን የኬንያ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ካሳወቀ በኋላ ድርድሮች መደረጋቸው ተዘግቧል። ዊሊያም ሩቶ 3 ሚሊየን የኬንያ ሽልንግ በአጋቾች መጠየቁን ገልፀው ሳሙኤል ይሰራበት የነበረው ድርጅት ክፍያውን መክፈሉን ገልጸዋል። ሳሙኤል ከተለቀቀ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ መቆየቱንና ወደ ኬንያ ሄዶ ከቤተሰቦቹ ጋር መቀላቀሉ ሲነገር ሩቶ ዜጎች…
Read More
ኢትዮጵያና ጅቡቲ ሁለተኛውን የኃይል መስመር ዝርጋታ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና ጅቡቲ ሁለተኛውን የኃይል መስመር ዝርጋታ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያን ጋላፊ ማከፋፈያ ጣቢያ ከጅቡቲው ናጋድ ማከፋፈያ ጣቢያ ጋር በሚያገናኘው በዚህ ፕሮጀክት፤ የ230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ እንደሚከናወን በጅቡቲ በተካሄደው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገልጿል፡፡ በጅቡቲ ግዛት የሚዘረጋውን 190 ኪሎ ሜትር ጨምሮ በአጠቃላይ 292 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የኃይል መስመር ፕሮጀክት በ18 ወራት ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙ ተዘግቧል፡፡ ዓለም ባንክ ዝርጋታውን በ55 ሚሊዮን ዶላር ብድር የሚደግፈው ሲሆን፤ የግንባታ ውሉ ትራንስሬይል ሊሚትድ ለተሰኘ የህንድ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ መሰጠቱን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡ የጅቡቲ የኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዲ፤ “ፕሮጀክቱ ታዳሽ የኃይል ሀብቶችን በመጠቀም ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ የኃይል ፖሊሲ እንድንተገብር ይረዳናል፣ ይህም 100 በመቶ የንጹህ ኃይል ግባችንን እንድናሳካ ያስችለናል” ሲሉ ተናግረዋል። የኃይል መስመር…
Read More
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል እና ዲኤስቲቪ በመተባበር ያዘጋጁት የጥበብ ምሽት ተካሄደ 

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል እና ዲኤስቲቪ በመተባበር ያዘጋጁት የጥበብ ምሽት ተካሄደ 

"የአንድ ግጥም አንድ ወግ" ኪነ ጥበባዊ ዝግጅት በድምቀት የተከናወነ ሲሆን በዲኤስቲቪ አቦል ቴሌቪዥን የሚተላለፉ ተወዳጅ ድራማዎችን እያቀረቡ ያሉት ተዋናዮችና ፕሮዲዩሰሮች የዝግጅቱ ልዩ እንግዶች በመሆን ልምዳቸውን አካፍለዋል።  የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ " በሀገራችን የኪነ ጥበብና በተለይም በቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም ስራዎች ጉልህ አበርክቶ እያከናወነ ካለው ዲኤስቲቪ አቦል ቴሌቪዥን ጋር በትብብር የጥበብ መድረክ ማዘጋጀታችን ወደፊትም ይቀጥላል። ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋርም በትብብር ለመስራት ባሕል ማዕከላችን ክፍት ነው" ሲሉ በመክፈቻ ዝግጅቱ ወቅት ተናግረዋል።  የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ የማርኬቲንግ ኃላፊ ወ/ሮ ትህትና ተስፋዬ በበኩላቸው " እኔ እና ዲኤስቲቪ" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የብራንድ ትውውቅ ከ አአዩ ባሕል ማዕከል ጋር መዘጋጀቱን ገልፀው አብዛኛው…
Read More
ሁለት ኢትዮጵያዊያን በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሁለት ኢትዮጵያዊያን በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያውያን አንድ ህንዳዊ በመግደል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል። የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት በቅርቡ በጂዳ ከተማ 'አንድ ህንዳዊ ዜጋ ላይ ተኩስ ከፍተው ገድለዋል' ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡ የጂዳ ግዛት ፖሊስ ባወጣው መግለጫ፤ የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት ደንቦች በመጣስ በሕገ-ወጥ መንገድ በሚኖሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ክስ መመስረቱን አስታውቋል። በከተማዋ አቅራቢያ በሚገኝ ተራራማ አካባቢ ሕገ-ወጥ ዕፅ በመገበያያት ላይ በነበሩ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ጠብና አለመግባባት ሳቢያ ህንዳዊው ግለሰብ በጥይት መመታቱን ገልፍ ኒውስ ዘግቧል፡፡ በዚህም በግጭቱ ወቅት ከተጠርጣሪዎቹ አንዱ ኢትዮጵያዊ በህንዳዊው ተጎጂ ላይ ተኩስ ከፍቶ ጉዳት እንዳደረሰበት የገለጸው ፖሊስ፤ በጥይት የተመታው ግለሰብ ወዲያውኑ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ቢወሰድም፣…
Read More
ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችው በህወሀት ምክንያት መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናገሩ

ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችው በህወሀት ምክንያት መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናገሩ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት አዛዥ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በሰሜን እዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ለማሰብ በሚል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ህወሀትን ተችተዋል። ፊልድ ማርሻል በዚህ ጊዜ እንዳሉት መከላከያ ሠራዊት ሕይወቱን ከሰጠለት ሕዝብ ውስጥ የወጡ ጥቂት ካሃዲዎች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከኋላው መውጋታቸው ሕመሙ ጥልቅ ነው ብለዋል። በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመው ክህደት ወንድም ወንዱሙ ላይ የፈፀመው ክህደት በመሆኑ በታሪክ ልዩ እንደሚያደርገውም ጠቅሰዋል። የትግራይ ሕዝብ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ክህደት አይቀበለውም ያሉት አዛዡ  የትግራይ ሕዝብ በልጆቹ ክህደት አፍሮ፣ ተመልሰን መቐለ ስንገባ አጨብጭቦ ተቀብሎን ነበር ሲሉም አክለዋል። ስለዚህ ክህደት እና አስነዋሪ ታሪክ ስናውራ ስለ ጥቂት የሕወሓት አመራሮች እንጂ ስለ ትግራይ ሕዝብ እንዳልሆነም ገልጸዋል። የህወሀት…
Read More
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙት ጥቃቶች እንዲመረመሩ ለዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ጥሪ ቀረበ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙት ጥቃቶች እንዲመረመሩ ለዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ጥሪ ቀረበ

አምስት ፓርቲዎች የመሰረቱት 'ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት' የተሰኘው ቅንጅት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙት ጥቃቶች እንዲመረመሩ ለዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ቅንጅቱ በቅርቡ  በአርሲ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤“ በኢትዮጵያ የሚፈጸሙት ማንነትና ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶች መንግሥታዊ መዋቅርን የተከተሉ፣ ሥርዓታዊና ተጨማሪ እጅ ያለበት ስለመኾኑ ምርመራ እንዲደረግ ” ጥሪውን አቅርቧል። ቅንጅቱ፤ “ጠያቂም ተጠያቂም ባለመኖሩ መግደል ቀላል ኾኗል” በሚል  ያወጣው መግለጫ፤ “ እንዲህ ዓይነቱን ግዙፍ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት" በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታውቆ፣ "እልቂት የየቀን ገጠመኙ ለኾነው የአካባቢው ማኅበረሰብም" ብርታትና መጽናናትን ተመኝቷል። መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ እናት ፓርቲ፣ አዲሲ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አኢዴፓ) እና አማራ ግዮን ንቅናቄ ( አግን) የመሠረቱት ' ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት…
Read More