19
Mar
ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ያለውን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዲሁም ሰዎችን ላላስፈላጊ ውፍረት የሚዳርገውን ከመጠን በላይ የሆነ የአመጋገብ ሥርዓትን የሚያጠና ነው ተብሎለታል። በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎችን እና የተለያዩ ችግሮችን መቋቋም የሚችሉ የምግብ ስርዓትን ለማቅረብ ያለመ መሆኑ የተነገረለት ይህ ፕሮግራም የአዲስ አበባ ነዋሪን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል። ፕሮግራሙ በከተሞች ላይ ያለው የስርዓተ ምግብ ምን ሁኔታ ላይ ነው፣ ምንስ መስተካከል አለበት የሚሉ እና ሌሎች ጥናቶችም እየከወነ ለፖሊሲ አውጭዎች እና ለሚመለከታቸው ተቋማት መረጃ የመስጠት ስራ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይሰራል ተብሏል። በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የስነ ምግብ እና የአካባቢ ጤና ዳይሬክተር ዶክተር ማስረሻ ተሰማ እንዳሉት ፕሮጀክቱ በከተማዎች ላይ ያለን የስርአተ ምግብ ሁኔታን እየተከታተሉ መረጃ…