02
Apr
በበፍቃዱ ኃይሉ ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ከኃይለማርያም ደሳለኝ ከተረከቡ ስድስት ዓመታት ተቆጠሩ። ዐቢይ በእነዚህ ዓመታት የተከተሉት የአመራር ሥልት በፍቃዱ ኃይሉ “እየሰጡ መንሳት” የሚለው አባባል ይገልጸዋል የሚል አተያይ አለው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን የሥልጣን ማማ ከተቆናጠጡ እነሆ ዛሬ መጋቢት 24፣ 2016 ስድስት ዓመት ሞላቸው። በዘመናዊ ፖለቲካ ከአንድ የአገር መሪ የሚጠበቁት መሠረታዊ ኃላፊነቶች ሰላም እና መረጋጋት ማስፈን፣ ሕግ እና ስርዓት ማበጀት እንዲሁም ሥራ መፍጠር እና ኢኮኖሚ ማረጋጋት ናቸው። እነዚህ ዘርፎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እምብዛም ናቸው። ይልቁንም በነውጥ እና ወጀብ እየተላጋች በምትሔደው መርከብ ውስጥ ወደ ካፒቴኑ መንበር ለመውጣት እርካቡ ላይ መንጠላጠል እንዲሁም መንበሩ ላይ ተደላድሎ መቀመጥ ግን ይችሉበታል። ይህንን…