wildanimal

በኢትዮጵያ የሚገኘው ባለ ጥቁር ጎፈር አንበሳ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

በኢትዮጵያ የሚገኘው ባለ ጥቁር ጎፈር አንበሳ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እንዳስታወቀው የኢትዮጲያው ጥቁር ጎፈር አንበሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እየተመናመነ በመምጣቱ የመጥፋት አደጋ ተጋረጦበታል ተብሏል፡፡ በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ህገወጥ ዝውውር ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ እንደተናገሩት ህገወጥ የነዋሪዎች ሰፈራ፣ የደን ጭፍጨፋ መኖር፣ የእርሻ ስራ እና  ግጦሽ  መበራከት የእንስሳቶቹ ስፍራ እንዲወድም ያደረጉ ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው። በዚህም አንበሳን ጨምሮ የዱር እንስሳት የሚፈልጉትን ምግብ እንዳያገኙና በምግብ ሰንሰለት ውስጥ ችግር እንዲፈጠር ብሎም ለህገወጥ አደን  በስፋት ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ሲሉ አክለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የተለየ የአንበሳ ዝርያ ነው ተብሎ የሚታወቀው እና የመጥፋት አደጋ ያጠላበት የጥቁር ጎፈር አንበሳ  ቆዳም በአብዛኛው  በኬንያ ፣በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን በኩል የህገወጥ ዝውውር …
Read More