wildlife

የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን 60 ሰራተኞቹ እንደተገደሉበት አስታወቀ

የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን 60 ሰራተኞቹ እንደተገደሉበት አስታወቀ

የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ባለፉት 60 ዓመታት ቢያንስ 60 ሠራተኞቹን በሥራ ላይ እያሉ ህይወታቸውን እንዳጡ ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ባለፉት 6 አሥርት ዓመታት የዱር እንስሳትን እና የተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅ ሂደት ውስጥ ቢያንስ 60 ሠራተኞቹ በሥራ ላይ እያሉ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አስታውቋል። ባለሥልጣኑ ዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የ60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን የፊታችን መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያከብር አስታውቋል። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ፣ ሠራተኞቹ ሕይወታቸውን ያጡት ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጋር በተያያዙ የተለያዩ የሥራ ላይ ፈተናዎች መሆኑን ገልጸዋል። ባለሥልጣኑ ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ ከ1 ሺህ 700 በላይ ለሚሆኑ ልዩ ልዩ የዱር እንስሳት ዝርያዎች ጥበቃ…
Read More
በኢትዮጵያ የሚገኘው ባለ ጥቁር ጎፈር አንበሳ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

በኢትዮጵያ የሚገኘው ባለ ጥቁር ጎፈር አንበሳ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እንዳስታወቀው የኢትዮጲያው ጥቁር ጎፈር አንበሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እየተመናመነ በመምጣቱ የመጥፋት አደጋ ተጋረጦበታል ተብሏል፡፡ በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ህገወጥ ዝውውር ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ እንደተናገሩት ህገወጥ የነዋሪዎች ሰፈራ፣ የደን ጭፍጨፋ መኖር፣ የእርሻ ስራ እና  ግጦሽ  መበራከት የእንስሳቶቹ ስፍራ እንዲወድም ያደረጉ ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው። በዚህም አንበሳን ጨምሮ የዱር እንስሳት የሚፈልጉትን ምግብ እንዳያገኙና በምግብ ሰንሰለት ውስጥ ችግር እንዲፈጠር ብሎም ለህገወጥ አደን  በስፋት ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ሲሉ አክለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የተለየ የአንበሳ ዝርያ ነው ተብሎ የሚታወቀው እና የመጥፋት አደጋ ያጠላበት የጥቁር ጎፈር አንበሳ  ቆዳም በአብዛኛው  በኬንያ ፣በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን በኩል የህገወጥ ዝውውር …
Read More
የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ከ200 ሄክታር በላይ መሬት ደን ወደመ

የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ከ200 ሄክታር በላይ መሬት ደን ወደመ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የሚገኘው የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ለእርሻ ኢንቨስትመንት በመሰጠቱ ከ200 ሄክታር በላይ የፓርኩ መሬት ደን ሙሉ ለሙሉ መውደሙን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የብሔራዊ ፓርኮች አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አዳነ ጸጋዬ፤ የባቢሌን የዝሆኖች መጠለያ ፓርክ በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን በኩል ለእርሻ ኢንቨስትመንት ተሰጥቶ ፓርኩ እየታረሰ በመሆኑ፣ በፓርኩ የሚገኙ ዝሆኖች ለአደጋ ተጋልጠዋል ብለዋል፡፡ የባቢሌን የዝሆኖች መጠለያ በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ድንበር ላይ የሚገኝ ሲሆን "በኦሮሚያ ክልል በኩል ያለው የፓርኩ ክፍል ለኢንቨስትመንት በመሰጠቱ አሁንም ድረስ እየታረሰ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። የፓርኩ መሬት ለኢንቨስትመንት የተሰጠው ፓርኮችን ለመጠበቅና ለማስተዳደር ኃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን…
Read More