11
Dec
በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የአንበሳ እና የስጋ በል እንስሳት ተመራማሪ የሆኑት አቶ ካህሳይ ገብረ-ተንሳይ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያሉት አንበሶች ቁጥር ከ1 ሺ እንደማይበልጥ ተናግረዋል። በሃገሪቱ አሁን ላይ አንበሶች ያሉበት ሁኔታ ለማወቅ ጥናት ማድረጋቸውን የገለፁልን ተመራማሪው በአዋሽ እና በመካከለኛው አዋሽ በተደረገው ጥናት መሰረት ያለው ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም አሁንም ግን ሁሉም ርብርብ ካላደረገ አንበሶቹን ልናጣ እንችላለን ብለዋል፡፡ ተመራማሪው እንደሚሉትም ህገወጥ የነዋሪዎች ሰፈራ፣ የደን ጭፍጨፋ መኖር፣ የእርሻ ስራ እና ግጦሽ መበራከት አንበሶቹ የሚፈልጉትን ምግብ እንዳያገኙና በምግብ ሰንሰለት ውስጥ ችግር እንዲፈጠር ብሎም ለህገወጥ አደን በስፋት ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብለዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የባህል መድኃኒት ቀማሚዎች ፊታቸውን ወደ አንበሳ አጥንት ማዞራቸው እንስሳቶቹን ለህገወጥ…