01
Mar
የደቡብ ሱዳን የወንዶች የቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈበት ማጣሪያው በዚህ ዓመት በሚካሄደው የዓለም ቅርጫት ኳስ ውድድር ለመሳተፍ ማለፍ በመቻሉ ታሪክ ሰራ። የደቡብ ሱዳን የቅርጫት ኳስ ቡድን በአፍሪካ የማጣሪያ ውድድር ውስጥ ሲሳተፍ የመጀመሪያው ቢሆንም ወደ ታላቁ ውድድር በመጀመሪያ ሙከራው በማለፉ በአፍሪካ የመጀመሪያው ሆኗል። ‘ብራይት ስታር’ እየተባለ የሚጠራው ቡድኑ በግብፅ አሌክሳንድሪያ በተደረገው ውድድር ሴኔጋልን 83 ለ 75 በመርታት በሚቀጥለው ነሐሴ በሚጀመረው እና ኢንዶኖኔዢያ፣ ጃፓን እና ፊሊፒንስ በጣምራ በሚያዘጋጁት የዓለም ቅርጫት ኳስ ዋንጫ እንደሚሳተፍ አረጋግጧል። በውድድሩ አፍሪካ በአምስት ብሔራዊ ብድን የምትወከል ሲሆን፣ አይቮሪ ኮስትም ቀደም ብላ ማለፏን አረጋግጣለች። እንደአውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2011 ከሱዳን ተለይታ ነጻ አገር ሆና የተመሠረተችው ደቡብ ሱዳን 11.5…