07
Mar
ዶናልድ ትራምፕ ቻይና 50 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል ጠየቁ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና 50 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ ልትከፍል ይገባል ብለዋል። የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውሀን ቤተ ሙከራ ውስጥ ማምለጡን የሚናገሩት ትራምፕ ቫይረሱ በአሜሪካ ላይ ላደረሰው ጉዳት ቻይና ካሳ እንድትከፍል ጠይቀዋል ሲል ዴይሊ ሜይል ዘግቧል። አሜሪካ በተደጋጋሚ የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ቤተ ሙከራ አምልጧል በሚል ስትናገር የሚሰማ ሲሆን ቻይና ግን ይህን ክስ ውድቅ አድርጋለች። የኮረና ቫይረስ በዓለም ላይ ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ሲገድል አሜሪካ፣ ብራዚል እና ሕንድ ብዙ ዜጎቻቸውን በሞት ያጡ ሀገራት ናቸው።