19
Apr
በሳሙኤል አባተ በኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ዓመታት በኮቪድ -19 ከ7 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታውቋል። በኢትዮጲያ በሶስት ዓመት ውስጥ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰው ሲጠቁ ከ7ሺህ 500 በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ። ባለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በኮቪድ -19 በሽታ 500 ሺ 774 ሰዎች ሲያዙ ከነዚህም ውስጥ 7ሺህ 574 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል ። የኮቪድ-19 ክትባት በሶስት ዙር የተሰጠ መሆኑንና የተፈናቀሉ እና እስረኞች የክትባት ተከታታይ ተጠቃሚነት ላይ ቁጥሩ ዝቅተኛ እንደሆነ በጤና ሚኒስቴር የክትባት ኤክስፐርት የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ አየለ ተናግረዋል ። በዓለም ላይ በኮቪድ -19 በሽታ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች እንደሚጠቁ…