18
Oct
ኩላሊት ከሞተ ሰው እንዲወሰድ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ከስድስት ዓመት በፊት የተዘጋጀ ቢሆንም እስካሁን መልስ እንዳላገኘ የኩላሊት ህመምተኞች ማህበር ተናግሯል፡፡ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ የኩላሊት ልገሳን ከቤተሰብ ውጭ እንዲለገስ የማይፈቅደው የኢትዮጵያ የጤና ህግ እንዲሻሻል ቢጠየቅም መልስ አለማግኘቱ ችግር እንደሆነ ተነግሯል። በቅርቡ በተወካዮች ምክር ቤት የጤና ህጎች ረቂቅ አዋጅ መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ስለ ኩላሊት ልገሳ የሚያወራው ህግ ግን እስካሁን እንዳልቀረበ በኩላሊት ተካሚዎች ማህበር በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ኩላሊት ከሞተ ሰው በቀዶ ህክምና ከበጎ ፈቃደኞች እንዲወሰድ የሚረዳ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ላለፉት ስድስት ዓመታት እየተጠየቀ ቢቀጠልም እስካሁን ተግባራዊ መሆን እንዳልተቻለም አስታውቀዋል። ከቤተሰብ የሚደረገው የልገሳ ሂደትም በለጋሽ…