08
Mar
መንግስት አራት ድርጅቶችን ወደግል ለማዛወር ማቀዱ ተገለጸ መንግስት የተወሰኑ ተቋማትን ወደግል የማዛወር እቅድ እንዳለው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃብታሙ ኃይለሚካኤል በሰጡት ማብራሪያ፤ በመንግስት የአክሲዮን ድርሻ ተይዘው ያሉ ተቋማት አሉ፡፡ እነርሱን ባለሃብቶች እንዲገቡበት ይፈለጋል ብለዋል፡፡ በመንግስትና በግል አጋርነት ያሉ እንደ ቢ.ኤም ጨርቃጨርቅ፣ አፍሪካ ጁስ፣ አብያታ ሶዳ አሽ እና አምቼ በሂደት ወደግል ባለሀብቶች ለማዛወር መታቀዱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። መንግስት ባለፉት ዓመትት 300 በላይ ድርጅቶችን ወደግል ማዛወሩን ጠቁመው፤በአሁኑ ወቅትም የመንግስትን እና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረገ መልኩ የነበረው አሰራር የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ…