01
Mar
ተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) በግጭት እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እርዳታ ጠባቂ ለሆኑ ኢትዮጵያውን ድጋፍ ለማድረግ ወደ አራት ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል አለ። ጽህፈት ቤቱ በአውሮፓውያኑ 2022 በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተፈጥሯዊ አደጋዎች እና በግጭት ምክንያት አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል ብሏል። ኦቻ ለዚህ የአውሮፓውያን ዓመት ባወጣው ‘የኢትዮጵያ ሰብዓዊ እርዳታ ዕቅድ’ በመላው አገሪቱ ለሚገኙ ከ20 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ድጋፍ ለማቅረብ 3.99 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። አስቸኳይ ዕርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች መካከል 4.6 ሚሊዮን የሚሆኑት የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መሆናቸው ተመላክቷል። በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጋላጭ ከሆኑ ቀዳሚ አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ፣ በአምስት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ከፍተኛ…