Divorce

በአዲስ አበባ የባለ ትዳሮች ፍቺ በ60 በመቶ ጨመረ

በአዲስ አበባ የባለ ትዳሮች ፍቺ በ60 በመቶ ጨመረ

በከተማዋ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከ4 ሺህ በላይ ትዳር መፍረሱ ተገልጿል የፈረሰው ትዳር ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በ60 በመቶ ጨምሯል ተብሏል በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት 4 ሺህ 696 ትዳር በፍቺ መጠናቀቁ ተገልጿል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የነዋሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሴ እንደገለፁት በ2015 ዓ.ም ከማዕከል እስከ ወረዳ ለ2 ሚሊየን 239 ሺህ 713 ተገልጋዮች አገልግሎት ተሰጥቷል። ከዚህ ውስጥ 37 ሺህ 397 ጋብቻ እና 4 ሺህ 696 ፍቺ መሆኑን ተናግረዋል። ዘንድሮ የተመዘገበው የፍቺ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር፥ የ60 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል። ለአብነትም በ2014 ዓ.ም 2 ሺህ 937 ፍቺ መመዝገቡን እና በ2015 ዓ.ም ወደ…
Read More
በአዲስ አበባ ባለፉት 6 ወራት ከ1ሺህ 300 በላይ ትዳር መፍረሱ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ባለፉት 6 ወራት ከ1ሺህ 300 በላይ ትዳር መፍረሱ ተገለጸ።

ባለፉት 6 ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ከ1ሺህ 300 በላይ ትዳር በፍቺ መጠናቀቃቸው ተገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 6 ወራት 1ሺህ342 ፍቺዎች እና 14ሺህ 136 ጋብቻዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል። ዘንድሮ በ6 ወራት ብቻ የተመዘገበው የፍቺ ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ተቀራራቢ ሲሆን፤ በ2014 በጀት ዓመት 1 ሺህ 623 የፍቺ ምዝገባዎች መደረጋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። በአዲስ አበባ ከ2012 እስከ 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 16 ሺህ 35 ፍቺዎች እንደተካሄዱ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል። የወሳኝ ኩነት ምዝገባና ማስረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ቤቴልሔም እንደሚገልጹት መረጃዎቹ የሚያመላክቱት በመስሪያ ቤቱ በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡትን ብቻ ነው።…
Read More