Blog

ከ18 ወራት በኋላ በሚካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክ 40 አገራት ያህል አድማ ሊመቱ ይችላሉ ተባለ

ከ18 ወራት በኋላ በሚካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክ 40 አገራት ያህል አድማ ሊመቱ ይችላሉ ተባለ

ከዓመት ከስድስት ወር በኋላ የሚካሄደውን የፓሪስ ኦሊምፒክ እስከ 40 አገራት ያክል አድማ ሊመቱ እንደሚችሉ ፖላንድ አስጠነቀቀች። የፖላንድ የስፖርት እና ቱሪዝም ሚኒስትር ካሚል ቦርትኒዙክ የፓሪስ ኦሊምፒክ ትርጉም አልባ ሊሆን ይችላል ብለዋል። ይህ የሚስትሩ አስተያየት የተሰማው ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ በፓሪሱ 2024 ኦሊምፒክ የሩሲያ እና ቤላሩስ ዜጋ አትሌቶች እንዲሳተፉ ለመፍቀድ ማቀዱን ፖላንድ፣ ሊቱኒያ፣ ኢስቶኒያ እና ላትቪያ በጋራ መቃወማቸውን ተከትሎ ነው። ዩክሬን የሁለቱ አገራት አትሌቶች የሚሳተፉ ከሆነ በውድድሩ አልገኝም ብላለች። የኦሊምፒክ ኮሚቴው ግን በውድድሩ ላይ አድማ ማድረግ ትርፉ “አትሌቶችን መቅጣት ብቻ ነው” ብሏል። የፖላንድ የስፖርት እና የቱሪዝም ሚንስትሩ የዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ከሳምንት በኋላ ከሚያደርገው ስብሰባ በፊት ግሬት ብሪቴን፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ካናዳን…
Read More
የኳታሩ ሼክ ጃሲም ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት መዘጋጀታቸውን አስታወቁ

የኳታሩ ሼክ ጃሲም ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት መዘጋጀታቸውን አስታወቁ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጉልህ ታሪክ ያለው እና በዘንድሮው የውድድር ዘመን ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት ባለሃብቶች ጥያቄያ አቅርበዋል። ከኳታር ትልልቅ ባንኮች የአንደኛው ሊቀ መንበር የሆኑት ሼክ ጃስሚ ቢን ሃማድ አል ታኒ ፋውንዴሽናቸው ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት ጥያቄ ማቅረቡን አረጋግጠዋል። ቢቢሲ መረዳት እንደቻለው የሰር ጂም ራትክሊፍ ንብረት የሆነው ኢኒዎስም ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው አሳውቋል። ቢሊዮነሩ ራትክሊፍ ማንችስተር ዩናይትድን የመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው ቀድመው አሳውቀው ነበር። በ2005 (እአአ) ማንችስተር ዩናይትድን የገዙት የግሌዘር ቤተሰቦች “ስትራቴጅክ አማራጮችን መፈለግ” በሚል ክለቡን ለመሸጥ አስበዋል። የኳታሩ ሼክ ጃሲም ክለቡን ወደ ቀድሞ ክብሩ የመመለስ ዕቅድ አለን በማለት ቡድኑን ቢገዙ ሊያደርጉ ያሰቡትን ገልጸዋል። የእግር ኳስ ቡድኑን ማጠናከር፣ የልምምድ…
Read More
በአፍሪካ የስፖርት ውድድሮች ላይ ዋነኛ አወዛጋቢ ጉዳይ የሆነው የዕድሜ ማጭበርበር

በአፍሪካ የስፖርት ውድድሮች ላይ ዋነኛ አወዛጋቢ ጉዳይ የሆነው የዕድሜ ማጭበርበር

ለዓመታት በአፍሪካ ስፖርት ላይ ጥቁር ጥላውን እንዳጠላ ነው። በቅርቡ በተካሄደው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ የችግሩ ስፋት ታይቷል። የስፖርተኞች የዕድሜ ጉዳይ። ካሜሩን ባዘጋጀችው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ ከነበሩት አገራት መካከል አንዷ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ነበረች። ነገር ግን ከጨዋታው ጅማሬ በፊት ከውድድሩ እንድትሰረዝ ተደርጓል። ምክንያቱ ደግሞ ለውድድሩ ከተላኩት ተጫዋቾች መካከል 25ቱ ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በላይ መሆናቸውን የኤምአርአይ ምርመራ በማሳየቱ ነው። ከኮንጎ በተጨማሪ ቻድ እንዲሁ ተጫዋቾቿን ካሜሩን ከላከች በኋላ ከውድድሩ ተሰርዛለች። የካሜሮን እግር ኳስ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ኤቶ የኤምአርአይ ምርመራ እንዲደረግ ካዘዘ በኋላ፣ ቻድ ለውድድሩ ካቀረበቻቸው ተጫዋቾች መካከል 30ዎቹ የዕድሜ ገደቡን አልፈዋል። በመላው ዓለም የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖችን የሚያማክሩት…
Read More
ደቡብ ሱዳን ለዓለም የቅርጫት ኳስ ዋንጫ በመጀመሪያ ሙከራዋ በማለፍ ታሪክ ሰራች

ደቡብ ሱዳን ለዓለም የቅርጫት ኳስ ዋንጫ በመጀመሪያ ሙከራዋ በማለፍ ታሪክ ሰራች

የደቡብ ሱዳን የወንዶች የቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈበት ማጣሪያው በዚህ ዓመት በሚካሄደው የዓለም ቅርጫት ኳስ ውድድር ለመሳተፍ ማለፍ በመቻሉ ታሪክ ሰራ። የደቡብ ሱዳን የቅርጫት ኳስ ቡድን በአፍሪካ የማጣሪያ ውድድር ውስጥ ሲሳተፍ የመጀመሪያው ቢሆንም ወደ ታላቁ ውድድር በመጀመሪያ ሙከራው በማለፉ በአፍሪካ የመጀመሪያው ሆኗል። ‘ብራይት ስታር’ እየተባለ የሚጠራው ቡድኑ በግብፅ አሌክሳንድሪያ በተደረገው ውድድር ሴኔጋልን 83 ለ 75 በመርታት በሚቀጥለው ነሐሴ በሚጀመረው እና ኢንዶኖኔዢያ፣ ጃፓን እና ፊሊፒንስ በጣምራ በሚያዘጋጁት የዓለም ቅርጫት ኳስ ዋንጫ እንደሚሳተፍ አረጋግጧል። በውድድሩ አፍሪካ በአምስት ብሔራዊ ብድን የምትወከል ሲሆን፣ አይቮሪ ኮስትም ቀደም ብላ ማለፏን አረጋግጣለች። እንደአውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2011 ከሱዳን ተለይታ ነጻ አገር ሆና የተመሠረተችው ደቡብ ሱዳን 11.5…
Read More
አንጋፋው ብስክሌተኛ ገረመው ደንቦባ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አንጋፋው ብስክሌተኛ ገረመው ደንቦባ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በኦሊምፒክ መድረክ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለመጀመሪያ ጊዜ በማውለብለብ ቀዳሚ የነበረው ብስክሌተኛ ገረመው ደንቦባ ባደረበት ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የብስክሌት ስፖርተኛው ገረመው ደንቦባ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት በ90 ዓመቱ ሕይወቱ ማለፉን ቤተሰቦቹ አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1956 ለመጀመሪያ ጊዜ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ በተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር ስትካፈል ከተሳተፉ ብስክሌተኞች ገረመው ደንቦባ አንዱ ነበር። ብስክሌተኛ ገረመው ደንቦባ በበርካታ የብስክሌት ውድድሮች ተሳትፎ ከ26 በላይ ዋንጫዎችን እና ከ32 በላይ ሜዳሊያዎችን ተሸልሟል። አትሌቱ በስፖርቱ ዘርፍ ላበረከተው ጉልህ አስተዋፅኦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሚያዘጋጀው የኢቢሲ ስፖርት አዋርድ 4ኛው የኢቢሲ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ሽልማት የሕይወት ዘመን ተሸላሚ አትሌት ነበር። ገረመው ደንቦባ ታኅሣሥ 7 ቀን 1925 ዓ.ም በአዲስ…
Read More
ባሏን የገደለችው ዝነኛዋ አትሌት ጉዳይ

ባሏን የገደለችው ዝነኛዋ አትሌት ጉዳይ

አትሌት በሱ ሳዶ ከሁለት ወንድሞቿ እና ከሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በመሆን ባለቤቷን በመግደል ወንጀል ተከሳ ድርጊቱን መፈጸሟ በመረጋገጡ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባት። በቅርበት የሚያውቋቸው የአዳማ አትሌቲክስ ክለብ አሰልጣኝ ሐብታሙ ግርማ ስለ ግድያው ሲናገሩ “እኔ በጣም ነው ያዘንኩት፤ በእርሱ ሞትም በጣም አዝኛለሁ። የእርሷም እስር ከሞት የማይተናነስ በመሆኑ እና አገሪቱም እንዲህ ዓይነት ሰው በማጣቷ በጣም ነው ያዘንኩት” ብለዋል። የአትሌት በሱ ሳዶ የቀድሞ አሰልጣኝ ስለ ሁኔታ ሲናገሩ የተፈጸመውን ወንጀል አምነው መቀበል እንዳዳገታቸው “እኔ አሁን ራሱ ይሄ ነገር እንዴት አንደተፈጠረ ሊገባኝ አልቻለም” ሲሉ ግራ መጋባታቸውን ገልጸዋል። የመካከለኛ እና የረዥም ርቀት ሯጯ አትሌት በሱ ሳዶ እንዲሁም አብሯት የነበረው ወንድሟ ከባለቤቷ ግድያ ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ሆነው…
Read More
ምስሉ በጅማ ከተማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ግለሰብ አመራር ቤት ውስጥ የተገኘን የጦር መሳርያ አያሳይም

ምስሉ በጅማ ከተማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ግለሰብ አመራር ቤት ውስጥ የተገኘን የጦር መሳርያ አያሳይም

የመጀመርያው ምስል የተለያዩ ጠመንጃዎችን የሚያሳይ ሲሆን ሁለተኛው ምስል የጥይት እና የጦር መሳርያ ምስሎችን ያሳያል። ሶስተኛው ምስል ደግሞ የጦር መሳርያ የተገኘበትን ግለሰብ ምስል ያሳያል በማለት አጋርቶት ነበር።  ከዚህም በተጨማሪ  ይህ የፌስቡክ ፖስት በምስሉ ላይ የተመለከተው ግለሰብ “በጅማ የማህበረ ቅዱሳን ማዕከል ሰብሳቢ እና የደብተራ መድሃንያለም ቤተክርስትያን ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ነው።” የሚል የመግለጫ ፅሁፍን አብሮ አያይዟል። ይህ የፌስቡክ ፖስት በብዙ ስዎች ዘንድ ተጋርቶ የነበረ ሲሆን ከ400 በላይ ግብረ መልሶችን ማግኘት ችሏል።  ይሁን እንጂ ምስሎቹ የቆዩ ሲሆኑ በፌስቡክ ገፁ የቀረበውን መረጃ እንደማይደግፉ ሀቅቼክ ማረጋገጥ ችሏል። በዚህም ምክንያት ሀቅቼክ መረጃውን ሀሰት ብሎታል።     በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት ከቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እውቅና ውጭ…
Read More
ምስሉ በአቡነ አብርሃም መኖርያ ቤት ውስጥ የተገኘ የጦር መሳርያን አያሳይም

ምስሉ በአቡነ አብርሃም መኖርያ ቤት ውስጥ የተገኘ የጦር መሳርያን አያሳይም

በጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም አንድ የትዊተር አካውንት ህገወጥ የጦር መሳርያዎች እና ጥይቶች በባህር ዳር ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ እና የፓትርያርኩ ፅ/ቤት አመራር በሆኑት በአቶ አቡነ አብርሃም መኖርያ ቤት ውስጥ ተገኝተዋል በማለት ሶስት ምስሎችን አጋርቶ ነበር። ይህ የትዊተር ፖስት በፖሊስ ፍተሻ ከአቡነ አብርሃም የመኖርያ ቤት ውስጥ አምስት ክላሽንኮቭ መሳርያዎች ከ235 ጥይት ጋር ተገኝቷል የሚል የመግለጫ ፅሁፍን አጋርቶ ነበር።   ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የትዊተር ፖስት ወደ አንድ መቶ ያህል ጊዜ መጋራት ችሎ የነበረ ሲሆን ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተመልክተውታል። ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉን ተመልክቶ መረጃውን እንደማይደግፍ በማረጋገጥ ሀሰት ብሎታል።  በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት ከቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እውቅና ውጭ የተለያዩ ጳጳሳትን…
Read More
ምስሉ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ አያሳይም

ምስሉ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ አያሳይም

የተለያዩ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የኦሮሚያ እና የሶማልያ ክልል አካባቢዎች ላይ ከባድ ድርቅ መከሰቱን ያሳያሉ። ይህ ድርቅ በእነዚህ አካባቢዎች ለአምስት ተከታታይ አመታት ተከስቷል። ይሁን እንጂ በነዚህ አካባቢዎች ከተከሰቱት ድርቆች መካከል በቦረና የተከሰትው ድርቅ ከባዱ ነው። በምስራቃዊ እና ደቡባዊ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በተለይም የቦረና አካባቢ ባለፉት አመታቶች ከባድ በሆነ ድርቅ የተጎዳ አካባቢ ነው። ከዚህ ድርቅ ጋር በተያያዘ በባለፈው አመት በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት ፤ ሴቶች እና አረጋውያን በምግብ እጥረት እና በድርቁ ምክንያት የቀንድ ከብቶቻቸውን በማጣታቸው ምክንያት ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋልጠው ነበር።  በአሁኑ ሰዓት በእነዚህ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ከአየር ንብረት መለዋወጥ እንዲሁም እነዚህ አካባቢዎች  ዝናብ በማጣታቸው ምክንያት የተከሰተ ነው።  ይህ ድርቅ ወደ…
Read More
ምስሎቹ ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸውን C-130 ሄርኩሊዝ የጦር አውሮፕላኖችን ያሳያል?

ምስሎቹ ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸውን C-130 ሄርኩሊዝ የጦር አውሮፕላኖችን ያሳያል?

አንድ የፌስቡክ ፖስት ግንቦት 7 ፤ 2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸው C-130 ሄርኩሊዝ ጀቶች የሚል ፅሁፍን አያይዞ አምስት ምስሎችን አጋርቶ ነበር። ይህ የፌስቡክ ፖስትም ከ44 ጊዜ በላይ ሲጋራ ከ500 በላይ ግብረ መልሶችንም ማግኘት ችሎ ነበር። ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉን አጣርቶ መረጃውን በከፊል ሀሰት ብሎታል።  በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት እስካሁን ድረስ ያልተፈታ ችግር ሆኗል።  ከጥቂት ወራት በፊት ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በሚል በፌደራሉ መንግስት የቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት በህወሓት ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ የነበረ ሲሆን ይህ ስምምነት ለሰላም ንግግር እና ግጭቱን ለማቆም ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ተገምቶ ነበር።  የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከታወጀ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና በህወሓት አመራር በሆኑት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መካከል የቀጥታ የስልክ ንግግር (ውይይት)…
Read More