drought

በኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 200 ሺህ ዜጎች መሞታቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 200 ሺህ ዜጎች መሞታቸው ተገለጸ

በፈረንጆች 2022 ብቻ በኢትዮጵያ በረሃብና በበሽታ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ በፈረንጆቹ 2022 ዓመት ብቻ በኢትዮጵያ በረሃብ እና ከረሀብ ጋር ተያይዘው ከሚከሰቱ በሽታዎች በተያያዘ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል። በዚህም በኢትዮጵያ በረሃብና ተያያዥ በሽታዎች የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለእርዳታ የሚልኩት እህል ለግል ጥቅም ሲውል እና በገበያ ላይ ሲሸጥ አረጋግጠናል በሚል የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጡም፣ በዚህ ወቅት በረሃብ እና በበሽታ ለሞቱ ሰዎች እንደ ዋና ምክንያት ተጠቅሷል። እንዲሁም በዚያው ዓመት በተፈጠሩ ግጭቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺሕ በላይ መሆኑን ግሎባል ፒስ ኢንዴክስ በድኅረ ገጹ አስነብቧል፡፡ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የእርስ በርስ ግጭት…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 331 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 331 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አደረገች። ለሥራ ጉብኝ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አድርገዋል። አንቶኒ ብሊንከን እንዳስታወቁት ድጋፉ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አማካኝነት የሚሸፈን ነው፡፡ ድጋፉም በተለያዩ ምክንያቶች በችግር ለተጋለጡ ወገኖች ለምግብ፣ ለመድሃኒት፣ ለንጹህ የመጠጥ ውሃ የሚውል መሆኑን ገልፀዋል። ይህም በግጭት ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ፣ በድርቅ ለተጠቁ እና ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ሕይወት አድን ድጋፍ ማድረግ ያስችላል ተብላል።
Read More