15
Mar
የፊታችን እሁድ መጋቢት 10 ቀን 2015 ዓ.ም የ2023 የሮም ማራቶን ይካሄዳል። በዚህም ማራቶን ታሪክ ራሱን ይደግማል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያዊው የባዶ እግር ሯጭ እንዲሁም ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ቁልፍ ዳይሬክተር በመሆን የሰራው የ45 ዓመቱ ኤርሚያስ አየለ ሙሉ ማራቶን በባዶ እግሩ ይሮጣል። ኤርሚያስ አየለ ይህንን የሚያደርገው ለኢትዮጵያው ታላቅ አትሌት አበበ ቢቂላ ክብር እንዲሁም ለሀገር ገፅታ ግንባታ ሲል ነው። " አበበ ቢቂላ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት የመጀመሪያው ጥቁር በመሆኑ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለአፍራካውያን ስኬት መሰረት ጥሏል " የሚለው ኤርሚያስ " ሆኖም ግን ለሰራው ታሪክ የሚገባውን ያህል እውቅና እንዳላገኘ ይሰማኝ ነበር " ብሏል። ኤርሚያስ ፤ የአትሌት አበበ ቢቃላ ታሪክ ሁሌም…