Merawi

አሜሪካ በመርዓዊ ከተማ የተፈጸመው የንጹሃን ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲመረመር ጠየቀች

አሜሪካ በመርዓዊ ከተማ የተፈጸመው የንጹሃን ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲመረመር ጠየቀች

ከአማራ ክልል ዋና ከተማ ከሆነችው ባህርዳር በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው መራዊ ከተማ ባሳለፍነው ሳምንት ከሰሞኑ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ ተቀስቅሶ ነበር፡፡ በዚህ ውጊያ ምክንያት የፋኖ ታጣቂዎች የመራዊ ከተማን ተቆጣጥረው የነበረ ቢሆንም በኋላ ለቀው መሄዳቸውን ተከትሎ ወደ ከተማው የገባው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ50 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎችን እንደገደሉ ቢቢሲ ነዋሪዎችን አነጋግሮ ዘግቧል፡፡ እንደ ነዋሪዎቹ አስተያየት ከሆነ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ነዋሪዎቹን ከመንገድ ላይ እና መኖሪያ ቤታቸው በማሰባሰብ ገድለዋቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በኢምባሲው ማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ባወጡት መግለጫ በመርዓዊ ከተማ የተፈጸመው የንጹሃን ዜጎች ግድያ እንደሚያሳስባቸው፣ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲመረመር ጠይቀዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ እና ኦሮሚያ…
Read More