Ethiopia

ኢትዮጵያ በግላስኮው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድርን በአምስተኛነት አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በግላስኮው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድርን በአምስተኛነት አጠናቀቀች

በስኮትላንድ ግላስጎ ሲካሄድ የቆየው የ2024 የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ፍጻሜውን አግኝቷል። ከየካቲት 22 እስክ 24 2016 ዓ.ም ሲካሄድ በነበረው የ19ኛው የዓለም የቤት ዉስጥ ሻምፒዮና ከ130 በላይ ሀገራት  የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶቸ  መሳተፋቸው ተነግሯል። ኢትዮጵያ በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር  በሴትና በወንድ  በአጠቃላይ  በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች መሳተፏን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በሻምፒዮናው በሴቶች 800 ሜትር ፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ የወርቅ፣ በሴቶች 3000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ የብር እንዲሁም በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች ሆነዋል። በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ  ሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር…
Read More
በባህር ዳር ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ከባድ ጦርነት መከሰቱ ተገለጸ፡፡

በባህር ዳር ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ከባድ ጦርነት መከሰቱ ተገለጸ፡፡

በአማራ ክልል መዲና ባህርዳር ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ከባድ ተኩስ ሲካሄድ እንደነበር ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡ ለደህንነታቸው የሰጉ እና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የባህርዳር ከተማ ነዋሪ እንዳሉን ከሆነ ከዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ የተኩስ ድምጽ መስማታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ነዋሪው አክለውም በፍርሃት ቤት ውስጥ በራቸውን ዘግተው ቤተሰባቸውን ይዘው መቀመጣቸውን የነገሩን እኝህ ነዋሪ በተለይም እስከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ መካሄዱንም ነግረውናል፡፡ ውጊው በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል መካሄዱን እርግጠኛ ነኝ የሚሉን እኝህ ነዋሪ ንጹሃን ከቤታቸው ባለሙውጣታቸው የከፋ ጉዳት እንዳላስተናገዱም አክለዋል፡፡ አሁን ላይ በተለይም ከምሳ ሰዓት ጀምሮ የውጊያ ድምጽ እየሰሙ እንዳልሆነ አንቡላንሶች በመንገዶች ላይ ሲመላለሱ መመልከታቸውንም ነግረውናል፡፡ ሌላኛው በባህር ዳር መሀል ከተማ…
Read More
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአራት ክልሎች ምርጫ ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአራት ክልሎች ምርጫ ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6 ኛውን ዙር ቀሪና ድጋሚ ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድባቸው አራት ክልሎች ምርጫ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡ ምርጫ የሚካሄደው በጸጥታ እና በሌሎች ምክንያቶች ምርጫ ያልተካሄደባቸው አካባቢዎች ነው የተባለ ሲሆን የቤንሻንጉል ጉምዝ፤ አፋር፤ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 29 የምርጫ ክልሎች ውስጥ እንደሆነም ቦርዱ አስታውቋል፡፡ በዚህ ምርጫ ፕሮግራም ለዘጠኝ የተወካዮች ምክር ቤትና ለሃያ ስድስት የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ለማካሄድ እንደታቀደም ተገልጿል፡፡ ቦርዱ ባወጣው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ መሰረትም የእጩዎች ምዝገባ ከሚያዝያ 7 እስከ ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ/ም ይካሄዳል የተባለ ሲሆን የምረጡኝ ቅስቀሳ ደግሞ ከሚያዚያ 7 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ይካሄዳል፡፡ እንዲሁም የመራጮች ምዝገባ ደግሞ ከሚያዝያ 7 እስከ…
Read More
ከ800 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት መሰደዳቸው ተገለጸ

ከ800 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት መሰደዳቸው ተገለጸ

ባለፉት አምስት ዓመታት ከ800 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት ፈልሰዋል የተባለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 78 በመቶ የሚሆኑት ወጣት ከመሆናቸውም በላይ አብዛኞቹ ሴቶች መሆናቸው ተነግሯል ። የኢትዮጵያ ዜጎች በስራ ዕድል እጦት የተነሣ በተለያዩ መተላለፊያዎች ድንበር አቋርጠው እንደሚፈልሱ የተገለፀ ሲሆን ድህነት ፣ የሰላም እጦት፣ የመነሻ ሐብት ምንጭ እጥረት ፣ የአየር ንብረት መለዋወጥና የተፈጥሮ ውድመት ዋና ዋና ገፊ ምክንያቶች እንደሆኑ ተገልጿል ። በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊያን ድንበር አቋርጠው እንዲፈልሱ ሳቢ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል ለራሳቸውና ቤተሰባቸው ገቢ የማመንጨት  ፍላጎት መኖር እና  የተሻለ ህይወት ፍለጋ እንደሆነ ይጠቀሳሉ ተብሏል ። የኢትዮጵያ ፍልሰተኛ ሰራተኞች ለኢትዮጵያ መልካም ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሲሆን ሀገሪቱ ውጭ ከሚኖሩና ከሚሰሩ ዜጎቿ ዳጎስ…
Read More
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ታንዛኒያን እንደሚጎበኙ ተገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ታንዛኒያን እንደሚጎበኙ ተገለጸ

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ኬንያ ያመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በናይሮቢ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተወያዩ ሲገለጽ የተለያዩ ተቋማትንም ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ኬንያ ሲጓዙ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያ እና ኬንያ ከ70 ዓመት በፊት ጀምሮ ጥብቅ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ከአንድ ሳምንት በፊትም የኢትዮ ኬንያ ሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ አካሂደዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ያለ ቪዛ ወደ ኬንያ እንዲሁም ኬንያዊያን ወደ ኢትዮጵያ ያለቪዛ እንዲገቡ የሚፈቅድ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ…
Read More
ኢትዮጵያ ለተረጂዎች ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልጋት ገለጸች

ኢትዮጵያ ለተረጂዎች ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልጋት ገለጸች

በኢትዮጵያ እያሻቀበ ላለው የተረጂዎች ቁጥር ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ መንግስት አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች የምግብ ርዳታ ለማቅረብ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ ባወጡት ሪፖርት ላይ አስታውቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ አታለለ አቡሃይ፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለው የተረጅዎች ብዛት 6 ነጥብ6 ሚሊዮን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተፈጥሮ አደጋዎች፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ጦርነት እና ሌሎች አደጋዎች ምክንያት የተፈናቃዮች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል፡፡ የብሪታንያ የአፍሪካ ልማት ዳይሬክተር በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ካደረጉ በኋላ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የ125 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም አሳሳቢ የምግብ…
Read More
ኑሮ ውድነት በመቀሌ ምን ይመስላል?

ኑሮ ውድነት በመቀሌ ምን ይመስላል?

በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት በቆየው ጦርነት ምክንያት ከተጎዱ ክልሎች መካከል አንዱ ትግራይ ሲሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ከመሞታቸው በተጨማሪ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ይህ ጦርነት በደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በተደረገው የፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ጦርነቱ የቆመ ሲሆን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ዳግም ስራ ጀምረዋል፡፡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ከተቋቋመ በኋላ ከፌደራል መንግስት እና ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ተጎጂዎችን ለመርዳት እየተሰራም ይገኛል፡፡ ቀስ በቀስ ህይወት በትግራይ ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶች እየተካሄዱ ሲሆን ኢትዮ ነጋሪ ወደ ክልሉ አምርታ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ምልከታ አድርጋለች፡፡ ከታዘብናቸው ጉዳዮች መካከል ህይወት በትግራይ መዲና መቀሌ ምን ይመስላል? የሚለው ሲሆን የኑሮ…
Read More
በባህርዳር 17 ንጹሃን ዜጎች በሀገር መከላከያ ሰራዊት ከህግ ውጪ መገደላቸው ተገለጸ

በባህርዳር 17 ንጹሃን ዜጎች በሀገር መከላከያ ሰራዊት ከህግ ውጪ መገደላቸው ተገለጸ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር ንጹሃንን ከህግ አግባብ ውጪ ገድሏል ብሏል። ተቋሙ በአማራ ክልል ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ሰፋ ያለ ሪፖርቱን አውጥቷል። በአቡነ ሃራ፣ ልደታ እና ሳባ ታሚት በተባሉ አካባቢዎች ከ17 በላይ ንጹሃን በመከላከያ ተተኩሶባቸው መገደላቸውን ከአይን እማኞች ማረጋገጡን የጠቆመው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አንዳንድ ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው ሰዎች አስከሬን መውሰድ እና መቅበር ተከልክለዋል ተብሏል፡፡ ሪፖርቱ በአማራ ክልል የመከላከያ ሰራዊትና የፋኖ ታጣቂዎች ውጊያ እንደጀመሩና ከሶስት ወር በኋላ በባህር ዳር ተፈጸሙ የተባሉ ግድያዎችን ብቻ የቃኘ ነው። የኢንተርኔት አገልግሎት መዘጋት እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስከተላቸው ክልከላዎች በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በዝርዝር…
Read More
በኢትዮጵያ ሶስት ቦታዎች በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በኢትዮጵያ ሶስት ቦታዎች በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በትናንትናው ዕለት በዱከም፣ በወላይታ እና ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በደረሱ ሶስት የትራፊክ አደጋዎች ምክንያት የ24 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ አደጋዎቹ የደረሱባቸው ኮሙንኬሽን ጽህፈት ቤቶች ባወጡት መረጃ መሰረት የትራፊክ አደጋዎቼ ሰቅጣጭ የሚባሉ ናቸው የተባለ ሲሆን በአጠቃላይ ከ24 ሰዎች ህይወት ማለፍ በተጨማሪ 20 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ዱከም ክፍለ ከተማ የደረሰው የትራፊክ አደጋ አንድ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከሁለት ሚኒባሶች እና አንድ ላንድ ክሮዘር ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው ደርሷል ተብሏል፡፡ በዚህ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 11 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በቢሾፍቱ ሆስፒታል በሕክምና ላይ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ ሌላኛው የትራፊክ አደጋ የተከሰተው በአዲሱ ማዕከላዊ…
Read More
በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ ስርጭት ወደ ከፋ ደረጃ መሻገሩን ክልሉ አስታወቀ

በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ ስርጭት ወደ ከፋ ደረጃ መሻገሩን ክልሉ አስታወቀ

በትግራይ ክልል ባለው አሁናዊ ሁኔታ የህጻናት የተጓዳኝ በሽታ መድኃኒት እና   የኤች አይ ቪ መመርመሪያ ኪት  እጥረት መኖሩን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አሰታወቀ፡፡ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የዘርፈ ብዙ ምላሽ የኤች አይ ቪ  መከላከል እና መቆጣጠር ስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፍሥሀ ብርሃነ ለትግራይ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከሶስት አመት በፊት በኤች አይቪ ስርጭት እና መቆጣጠር የተሻለ ጤና  አፈፃፀም ነበረው ብለዋል። አሁን ላይ ግን  የኤችአይቪ ስርጭቱ ወደ ከፋ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል። በፀጥታ እጦት ወቅት በርካታ ሴቶች እና እናቶች የመደፈር አደጋ ተጋላጭ በመሆናቸው  እንዲሁም መድኃኒት ተጠቃሚ የነበሩ ሰዎችም በመድሀኒት እጥረት በማቋረጣቸው  ለበሽታው ስርጭት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የክልሉ ጤና ቢሮ ባደረገው ጥናት…
Read More