12
Oct
የዘር ፍሬ ልገሳን የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ “የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ” በሚል ርዕስ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ አስራ ሁለት ክፍሎች ያሉት ረቂቅ አዋጁ ስለ አጠቃላይ የጤና አገልግሎት፣ ስለ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች፤ ስለ ጤና ዘርፍ የሰው ኃብት ልማት እና አስተዳደር፤ ስለ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ቁጥጥርን የሚመለከቱ 60 አንቀጾች አሉት። ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች የሚያወሳው የአዋጁ አራተኛ ክፍል ከዘረዘራቸው የጤና አገልግሎቶች መካከል አንዱ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ነው። በዚህ ንዑስ ክፍል ሥር የተካተተው አንቀጽ “ፈቃድ የተሰጠው የጤና ተቋም በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ የሕክምና አገልገሎት ሊሰጥ ይችላል” ሲል ሕክምናው…