IVF

በኢትዮጵያ የወንዴ የዘር ፍሬ መለገስ እንደማይቻል ተገለጸ

በኢትዮጵያ የወንዴ የዘር ፍሬ መለገስ እንደማይቻል ተገለጸ

ከሰሞኑ በትግራይ ክልል ወንዶች የዘር ፍሬያቸውን ሴቶች ደግሞ እንቁላላቸውን መለገስ እንደሚቻል የሚያሳይ ዘገባ መሰራቱ ይታወሳል፡፡ ቢቢሲ አማርኛ እንደዘገበው ከሆነ መሰረቱን በትግራይ ክልል መዲና መቀሌ ከተማ ያደረገ አንድ የህክምና ተቋም የወንድ ዘር ፍሬያቸውን ለሚለግሱ 10 ሺህ ብር እንዲሁም እንቁላላቸውን ለሚለግሱ ሴቶች ደግሞ 30 ሺህ ብር እንደሚከፍል አስታውቋል፡፡ ይህ የህክምና ተቋም ልጅ መውለድ ያልቻሉ ሰዎችን ጥያቄ መመለስ የሚያስችል ህክምና መጀመሩን እና ለዚህም የተለያዩ መስፈርቶችን አስቀምቷል፡፡ የጤና ሚኒስቴርን በጉዳዩ ዙሪያ እንዳለው ኢትዮጵያ ከበጎ ፈቃደኞች በተለገሱ የዘር ፍሬዎች አልያም እንቁላል ልጅ እንዲወለዱ የሚፈቅድ ህግ እንደሌላት አስታውቋል፡፡ በሚኒስቴሩ የጤና እና ጤና ነክ ተቋማት እና ባለሙያዎች ቁጥጥር ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ጸዳል ለአልዐይን እንዳሉት ኢትዮጵያ…
Read More