Kinfedagnawe

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና አብዲ ኢሌ ከእስር ተፈቱ

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና አብዲ ኢሌ ከእስር ተፈቱ

በ2013 በተካሄደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ታስረው ነበር፡፡ ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ እንዳሉት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በመታወቂያ ዋስትና ከእስር ተለቀዋል። የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ከሁለት ወራት በፊት በጸጥታ ሀይሎች ተይዘው የታሰሩ ቢሆንም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቆይተው ዛሬ ከእስር ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል። ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ በተመሳሳይ ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጽታ ሀይሎች ተወስደው በእስር ላይ የነበሩት ሌላኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብታቸው ከታሰሩ ከሰባት…
Read More