02
Oct
ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው አምንስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል ዋና ዋና ከተሞች አዲስ እስር እየተካሄደ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ከመስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የመንገስት የጸጥታ ሀይሎች ዜጎችን ከህግ ውጪ እየያዙ እያሰሩ መሆኑንም ተቋሙ በሪፖርቱ ለይ ጠቅሷል፡፡ በአምንስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ትግሬ ቻጉታህ እንዳሉት “የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ንጹሃንን ከህግ ውጪ በዘመቻ ማሰር መጀመራቸው መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ፍላጎት እንደሌለው ማሳያ ነው” ብለዋል፡፡ ተቋሙ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ባወጣው በዚህ ሪፖርቱ ላይ እንደገለጸው ለእስር የተዳረጉ ንጹሃን ህጉ በሚፈቅደው መሰረት በ48 ሰዓት ውስጥ ወደ ፍርድ ቤት እየቀረቡ አለመሆኑንም አስታውቋል፡፡ መንግስት ጀመረው በተባለው የዘመቻ እስር በክልሉ ባሉ ከተሞች የሚገኙ መምህራን እና…